SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ - podcast cover

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Last refreshed:
Follow this podcast in the Metacast mobile app to refresh it and see new episodes.
Download Metacast podcast app
Podcasts are better in Metacast mobile app
Don't just listen to podcasts. Learn from them with transcripts, summaries, and chapters for every episode. Skim, search, and bookmark insights. Learn more

Episodes

የእናቶች ቀን 2024፤ ትውልደ-ኢትዮጵያውያን እናቶችና ልጆች በአውስትራሊያ

ሐዌሪ ድንቄሳ (ከሲድኒ)፣ ፀሐይ በየነ (ከሜልበርን) እና ኤስሮት ሐብታሙ (ከብሪስበን)፤ የእናቶች ቀን አከባበርን፣ ለእናቶቻቸው ያላቸውን ፍቅርና ዕለተ በዓሉን እንደምን እንዳሳለፉ ይናገራሉ። ለመላ እናቶች መልካም ምኞታቸውን ይገልጣሉ።

May 13, 20249 min

የእናቶች ቀን በሀገረ አውስትራሊያ

በሜልበርን የተከበረውን የእናቶች ቀን አስመልክቶ ወ/ሮ ነጁም አብደላ ፤ ወጣት ባህጃ አብደይ ፤ ወ/ሮ መሊካ መሐመድ ፤ አርቲስት ሰብለ ግርማ ፤ ወ/ሮ ፍርዱስ ዪሱፍ እና ወ/ሮ ተወድዳ ዩሱፍ ዕለቱ ለእናቶችና ለማኅበረሰብ ስላለው ፋይዳዎች ይናገራሉ። የመልካም ምኞት መልዕክቶቻቸውንም ያስተላልፋሉ።

May 12, 202412 min

Navigating the implicit right to protest in Australia - አውስትራሊያ ውስጥ ስውር የተቃውሞ መብትን ማሰስ

Every week, impassioned Australians take to the streets, raising their voices in protest on important issues. Protesting is not an offence, but protesters sometimes test the limits of the law with extreme and antisocial behaviour. The chance of running into trouble depends on where you’re protesting and how you behave. - በየሳምንቱ ስሜታቸው የገነፈለ አውስትራሊያውያን ጎዳናዎች ላይ ወጥተው ጠቃሚ የሆኑ ጉዳዮችን አንስተው ድምፆቻቸውን ያሰማሉ። ተቃውሞን ማሰማት ጥፋት አይደለም፤ ይሁንና አልፎ አልፎ ተቃዋሚዎች ፀረ ማኅበራዊና ፅንፈኛ በሆነ ሁኔታ የሕግን ወሰን ይጋፋሉ። እራስን ለችግር መዳረጉ እንደ ...

May 09, 20248 min

የበዓለ ትንሣኤ አከባበር በአገረ አውስትራሊያ

ወ/ሮ ሰላማዊት ታደሰ (ከፐርዝ)፣ ዘውዴ ተስፋማሪያም (ከብሪስበን) እና አቶ ወንድወሰን ሽቱ (ከሜልበርን) እንደምን የፋሲካ በዓልን ከቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር እንዳሳለፉ ይናገራሉ። ለመላ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን መልካም ምኞታቸውን ይገልጣሉ።

May 08, 20249 min

"የባና ርዕይ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ለዓለም ገበያ ማቅረብና የኢትዮጵያን ባሕል በሉላዊ መድረክ ላይ እንዲያንፀባርቅ ማስቻል ነው" ድምፃዊትና ሥራ አስኪያጅ ብሌን መኮንን

የባና ሙዚቃ አሳታሚ መሥራች፣ ድምፃዊትና ዋና ሥራ አስፈፃሚት ብሌን መኮንን፤ ስለ ባና አመሠራረትና ሚና ታስረዳለች፣ ድምፃዊ ዕብነ ሐኪም እንደምን ወደ ሙዚቃ ዓለም እንደዘለቀና ስለመጪ የሙዚቃ አልበሙ "ብራና" ይናገራል።

May 08, 20245 min

"የአድዋ ጀግኖች ራሳቸውን መስዋዕት ያደረጉት ለእንጀራና ቡና አይደለም፤ የተለያየ ዘርና ሃይማኖት ላለው ሕዝብ ነፃነት ነው" ድምፃዊት ቤቲ ጂ

"ሽልማት ማለት ሥራችሁን ጨርሳችኋል፤ አቁሙ ማለት አይደለም። ለኒሻን ሲሆን ደግሞ ለሀገር ገና ብዙ ትሠራላችሁ የሚል አደራም ጭምር ነው" የምትለዋ ድምፃዊት፣ የሰብዓዊ ረድዔትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ማንነት አጉሊ ድምፅ ብሩክታይት ጌታሁን "Betty G"፤ ሰሞኑን ከኢትዮጵያ የዘውድ ምክር ቤት ስለተበረከተላት የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ ኒሻንና ሀገራዊ አንድነት ፋይዳዎች ትናገራለች።

May 07, 202420 min

“ የክርስቶስ ትንሳኤ ሞት የተሸነፈበት ታላቅ የምስራች የተሰበከበት ቀን ነው ። ” - መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሌ

መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያ የምስራቅ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ አሕጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ እንዲሁም የብሪስበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የፋሲካ በዓል መልዕክት፡፡

May 05, 202410 min

"ሎሬየት ፀጋዬ ገ/መድኅን የሀገር ዋርካ የሆነ አይተኬ ድንቅ የፈጠራ ሰው ነው፤ እንደ ፀጋዬ ያለ ሰው በምዕተ ዓመት ውስጥ የሚፈጠረው አንዴ ነው" አበራ ለማ

ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ፤ በድምፃዊ ጌታቸው ካሣ ተዘፍኖ ዘመን ተሻጋሪ ስለ ሆነው "ሀገሬን አትንኳት" ግጥሙ፣ ስለ ባለ ቅኔ ሎሬየት ፀጋዬ ገብረመድኅን ዘርፈ ብዙ ተጠባቢነትና ወዳጅነት አንስቶ ይናገራል። ሥነ ግጥሞቹንም ያስደምጣል።

May 04, 202418 min

"ጋዜጠኛ በንፁህ ኅሊናው ሚዛናዊ የጋዜጠኛነት ሥራን መሥራት እንጂ፤ ሙያውን የሚያራክስ ነገር መሥራት የለበትም። አሁን እንደወረርሽኝ የወረረን እሱ ነው" አበራ ለማ

ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ፤ የአገረ ኢትዮጵያን የራዲዮ ስርጭት፣ የጋዜጣ ሕትመት ውጤቶችንና የባለ ሙያዎቹን የሥነ ምግባር ደረጃ መዝኖ ግለ አተያዩን ያጋራል።

May 04, 202414 min

አበራ ለማ፤ ከመምህርነት ወደ ጋዜጠኛነትና ደራሲነት

ከኢትዮጵያ አንጋፋና ስመ ገነን ጋዜጠኞችና ደራሲዎች ውስጥ ቀዳሚ ተጠቃሽ ከሆኑቱ ውስጥ አበራ ለማ አንዱ ነው። በማስታወቂያ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ራዲዮና አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ በግሉ ፕሬስ በአዕምሮ ጋዜጣ የጋዜጠኛነት ድርሻውን አበርክቷል። በድርሰት በረከቶቹም ሰሞነኛውን "የዓለማችን ምስጢራት" መፅሐፉን አክሎ ከ20 በላይ መፅሐፍትን ለተደራሲያን እነሆኝ ብሏል።

May 03, 202412 min

Understanding the profound connections First Nations have with the land - ነባር ዜጎች ከመሬታቸው ጋር ያላቸውን ጥልቅ ቁርኝቶች መረዳት

The land holds a profound spiritual significance for Aboriginal and Torres Strait Islander peoples, intricately intertwined with their identity, belonging, and way of life. - ለአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች መሬት ጥልቅ መንፈሳዊ ፋይዳን የያዘ፣ ከማንነታቸው፣ ውሁድነትና የአኗኗር ዘዬ ጋር ተጋምዶ የተቆራኘ ነው።

May 02, 20247 min

“ ግላኮማን አንዴ ከተከሰተ ባለበት ማቆም እንጂ ሙሉ ለሙሉ ማዳን አይቻልም ” - ዶ /ር ለምለም ታምራት

ዶ /ር ለምለም ታምራት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ የዓይን ሐኪምና የግላኮማ ስፔሽያሊስት (ልዩ ሐኪም ) የዓይን ውስጥ ዕብጠት ግላኮማ ምንም አይነት ምልክቶችን ሳያሳይ ዕይታችንን ሊጋርድ የሚችል በሽታ መሆኑን ያስረዳሉ።

Apr 30, 202417 min
For the best experience, listen in Metacast app for iOS or Android