SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ - podcast cover

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Last refreshed:
Follow this podcast in the Metacast mobile app to refresh it and see new episodes.
Download Metacast podcast app
Podcasts are better in Metacast mobile app
Don't just listen to podcasts. Learn from them with transcripts, summaries, and chapters for every episode. Skim, search, and bookmark insights. Learn more

Episodes

Australia’s coffee culture explained - የአውስትራሊያ የቡና ባሕል ሲገለጥ

Australians are coffee-obsessed, so much so that Melbourne is often referred to as the coffee capital of the world. Getting your coffee order right is serious business, so let’s get you ordering coffee like a connoisseur. - አውስትራሊያውያን አቅላቸው ለቡና የማለለ ነው፤ ተዘውትሮም ሜልበርን የዓለም የቡና መዲና በሚል ተቀጥላ ትጠቀሳለች። ቡናዎን በውል ማዘዝም ሁነኛ ጉዳይ ነው፤ ልክ ቡናን በማጣጣም ክህሎት እንደተላበሰ ባለሙያ ቡናዎን እንዘዝልዎት።

Jun 07, 20248 min

"ከእነ ልጆቻችን መጠለያ የለንም፤ እባካችሁ ከቻላችሁ ጋራዣችሁን ወይም ጓሯችሁን ለድንኳን መትከያ ፍቀዱልን" አቶ ጊቤ ዘለቀና ወ/ሮ መቆያ ታምራት

ከአራት ሕፃናት ልጆቻቸው ጋር መጠለያ አጥ ሆነው ለጎዳና የተዳረጉት የሜልበርን - አውስትራሊያ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን አቶ ጊቤ ዘለቀና ወ/ሮ መቆያ ታምራት፤ ከኪራይና ጥገኛ ደባልነት አልፈው ለድንኳን ነዋሪነት ተዳርገዋል። ለኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት የድጋፍ ተማፅኖአቸውን ያቀርባሉ።

Jun 04, 202414 min

"የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግፎ እዚህ አድርሶኛል፤ ከአውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ የምሻው 'አይዞህ' የሚል የሞራል ድጋፍ ነው" ለማ ክብረት

በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅት የቀድሞው ዝነኛ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በረኛ ለማ ክብረት፤ ከውልደት እስከ ዕድገት፣ ከቁስቋም የሶስተኛ ክፍል እግር ኳስ ተጫዋችነት እስከ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂነት እንደምን እንደ ደረሰ አውግቷል። በቀጣዩ ትረካው ከሞሪሽየስ ጥገኝነት ጥየቃ እስከ አውስትራሊያ ዳግም ሠፈራ ያለ የሕይወት ጉዞውን ነቅሶ ያወጋል።

Jun 02, 202414 min

ለማ ክብረት፤ ከቁስቋም እስከ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን በረኛነት

ለማ ክብረት፤ በቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ባልደረባው ኤርሚያስ ወንድሙ አንደበት "ምናልባትም ከዓለም ምርጥ በረኛ" የተሰኘ፤ ሞሪሽየስ ላይ ከአምስት የመለያ ፍፁም ቅጣት ምቶች አራቱን በማዳን የሀገሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለድል ያበቃ ስመ ጥር ግብ ጠባቂ ነው።

Jun 02, 202415 min

"የቀድሞው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቡድ ግብ ጠባቂ ለማ ክብረት ወገን አለኝ እንዲል፤ላበረከተው አገልግሎት ተሰባስበን እናመስግነው"ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛውና አቶ ኤርሚያስ ወንድሙ

"ለማ ክብረት በዓለም ላይ ምርጥ ግብ ጠባቂ ሊሰኝ የሚችል፤ ቅን፣ ሰው አክባሪና የታመመን ጠያቂ ነው" የሚሉት የቀድሞው የለማ ክብረት የብሔራዊ ቡድን ባልደረባ አቶ ኤርሚያስ ወንድሙና "ለሀገራቸው ያገለገሉ የማኅበረሰብ አባላትን ዕውቅንና ከበሬታ ልንቸራቸው ይገባል" የሚሉት በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ ቅዳሜ ሰኔ 1 / ጁን 8 በሜልበር ስለሚካሔደው የሕይወት ዘመን አገልግሎት ልዩ የዕውቅና ፕሮግራም ያስረዳሉ፤ የግብዣ ጥሪና ምስጋናም ለማኅበረሰብ አባላት ያስተላልፋሉ።

Jun 01, 202413 min

"የዛጉዌ መንግሥት ዋነኛው የውድቀት ምንጭ የስልጣን ወራሾች ያደረሱት የእርስ በእርስ ቀውስ ነው" ዶ/ር ደረሰ አየናቸው

ዶ/ር ደረሰ አየናቸው፤ የቀድሞው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ዲን፣ የታሪክ ተባባሪ ፕሮፌሰርና በኤይክስ ማርሴል ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ ዘመን የአፍሪካ ቀንድ ጥናትና ምርምር ፕሮግራም ተመራማሪ ናቸው። ሰሞኑን በፀሐይ አሳታሚ ድርጅት አማካይነት ባበቁት "ታሪከ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፤ ከንጉሥ ዘርአ ያዕቆብ እስከ ንጉሥ ናኦድ (1426-500) መፅሐፋቸው ውስጥ ተካትተው ያሉትን የንጉሥ እስክንድር፣ አምደ ፅዮንና ናኦድ ዘመነ መንግሥታት አንስተው ይናገራሉ።

May 31, 202414 min

"አፄ ዘርአ ያዕቆብ 'መንግሥቴን በሃይማኖታችሁ መለያየት መክፈል አይቻልም' ብለው ደንግገው ነበር" ዶ/ር ደረሰ አየናቸው

ዶ/ር ደረሰ አየናቸው፤ የቀድሞው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ዲን፣ የታሪክ ተባባሪ ፕሮፌሰርና በኤይክስ ማርሴል ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ ዘመን የአፍሪካ ቀንድ ጥናትና ምርምር ፕሮግራም ተመራማሪ ናቸው። ሰሞኑን በፀሐይ አሳታሚ ድርጅት አማካይነት ባበቁት "ታሪከ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፤ ከንጉሥ ዘርአ ያዕቆብ እስከ ንጉሥ ናኦድ (1426-500) መፅሐፋቸው ውስጥ ተካትተው ያሉትን የንጉሥ ዘርአ ያዕቆብና ንጉሥ በዕደማርያምን ዘመነ መንግሥታት አንስተው ይናገራሉ።

May 31, 202410 min

"የመፅሐፉ ዋነኛ ዓላማ የታሪኩ ባለቤትና ቅርስ ወራሽ ከሆኑት ኢትዮጵያውያን ጋር ማገናኘት ነው" ዶ/ር ደረሰ አየናቸው

ዶ/ር ደረሰ አየናቸው፤ የቀድሞው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ዲን፣ የታሪክ ተባባሪ ፕሮፌሰርና በኤይክስ ማርሴል ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ ዘመን የአፍሪካ ቀንድ ጥናትና ምርምር ፕሮግራም ተመራማሪ ናቸው። ሰሞኑን በፀሐይ አሳታሚ ድርጅት አማካይነት ለሕትመት ስላበቁት "ታሪከ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፤ ከንጉሥ ዘርአ ያዕቆብ እስከ ንጉሥ ናኦድ (1426-500) መፅሐፋቸው ዋነኛ ይዘቶች ያስረዳሉ።

May 30, 202417 min

Should you consider private health insurance? - የግል የጤና ኢንሹራንስ ለመግባት ይሻሉን?

Australians have access to a quality and affordable public healthcare system. There's also the option to pay for private health insurance, allowing shorter waiting times and more choices when visiting hospitals and specialists. - አውስትራሊያውያን ጥራትና ለአቅም መጣኝ የሆነ የሕዝብ ጤና ክብካቤ ሥርዓት አላቸው። እንዲሁም፤ ሆስፒታሎችንና ስፔሻሊስቶችን ሲጎበኙ አጭር የቆይታ ጊዜን የሚያመቻችልዎና ተጨማሪ ምርጫዎች የሚፈቅድልዎ አማራጭ የግል የጤና ኢንሹራንስም አለ።

May 28, 20249 min

"በእኔ በኩል ቀጣዩ ሕይወቴ አውስትራሊያ ይሁን ኢትዮጵያ አላውቅም" ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ

በአንድ የጀርመን ባለስልጣን "ሰርከስ ኢትዮጵያ ጀርመን ውስጥ ኮካ ኮላ የሚታወቀውን ያህል በልጆች ዘንድ ይታወቃል" የተባለለት ድርጅት ዳይሬክተር የነበረው ዐቢይ አየለ፤ ስለ ጥገኝነት ጥየቃ ውጣ ውረዶችና የአውስትራሊያ ሕይወት ጉዞ ጅማሮው ይናገራል።

May 26, 202418 min

"ከ30 የሰርከስ ኢትዮጵያ አባላት ውስጥ 15ታችን አውስትራሊያ ጥገኝነት ጠይቀን ቀረን" ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ

የቲአትርና ፊልም ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ፤ በቀዳሚ ክፍለ ዝግጅታችን ስለ ትውልድና ዕድገቱ፣ የቀለም ትምህርትና የጥበብ ዕውቀት ቀሰማውን ከሰርከስ ኢትዮጵያ መቀላቀሉ ጋር አሰናስሎ አንስቷል። በሀገረ አውስትራሊያ የጥገኝነት ጥየቃው ውሳኔውን አስከትሎ ያወጋል።

May 26, 202414 min

What were the Australian Wars and why is history not acknowledged? - የአውስትራሊያ ጦርነቶች ምን ነበሩ፤ ታሪክ ዕውቅና ያልቸራቸው ስለምን ነው?

The Frontier Wars is a term often used to describe the more than 100 years of violent conflicts between colonial settlers and the Indigenous peoples that occurred during the British settlement of Australia. Even though Australia honours its involvement in wars fought overseas, it is yet to acknowledge the struggle that made it the country it is today. - የሠፋሪና ነባር ዜጎች ጦርነቶች ቃሉ በእንግሊዝ የአውስትራሊያ ሠፈራ ወቅት ከ100 ዓመታት በላይ በቅኝ ገዢ ሠፋሪዎችና በነባር ዜጎች መካከል የተካሔዱ ግጭቶችን ለመግለጥ ተዘውትሮ ይነገራል። ምንም እንኳ አውስትራሊያ የተሳተፈችባቸ...

May 24, 202413 min

“ በጥቃቅን እና አነስተኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የተሻለ ብድርን ለማግኘት ቀረጥን በአግባቡ መክፈል ይኖርባቸዋል። “ - አቶ እስቅያስ መንግስቴ

አቶ እስቅያስ መንግስቴ የፋይናንስ የብድር ማስፈቀድ እና ማመቻቸት ስራ ባለሙያ ፤ በአውስትራሊያ በኤን ዜድ ባንክ ለ 14 አመታት ያገለገሉ ሲሆን በአሁን ሰአት ከሌሎች መሰል ባለሙያዎች ጋር በመሆን በግል የብድር ማስፈቀድ እና ማመቻቸት ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ። በተለይ ደግሞ ወደ ግሉ ተቋም የዞሩብት ምክንያት ለሚኖሩትበት የማህበረሰብ አባላት ብድርን በማስገኘት እና በማማከር ረገድ በበለጠ ለማገልገል ነው ይላል።

May 21, 202415 min

"ተበዳሪዎች ብድርን ለማመልከት ከመሄዳቸው በፊት የተለያዩ አበዳሪ ተቋማት ያላቸው ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ጥናት ማድረግ አለባቸው ። " - አቶ እስቅያስ መንግስቴ

አቶ እስቅያስ መንግስቴ የፋይናንስ የብድር ማስፈቀድ እና ማመቻቸት ስራ ባለሙያ ፤ በአውስትራሊያ በኤን ዜድ ባንክ ለ 14 አመታት ያገለገሉ ሲሆን በአሁን ሰአት ከሌሎች መሰል ባለሙያዎች ጋር በመሆን በግል የብድር ማስፈቀድ እና ማመቻቸት ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ። በተለይ ደግሞ ወደ ግሉ ተቋም የዞሩብት ምክንያት ለሚኖሩትበት የማህበረሰብ አባላት ብድርን በማስገኘት እና በማማከር ረገድ በበለጠ ለማገልገል ነው ይላል።

May 21, 202414 min

ሁለት ዋነኛ የኑሮ ውድነት መቋቋያሚያ ዘዴዎች ምንድናቸው?

ዶ/ር ዮናታን ድንቁ - በአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት ተመራማሪ፤ የዘንድሮውን 2024/25 የአውስትራሊያ በጀት የትኩረት አጀንዳዎችና ፋይዳዎች አንስተው ያስረዳሉ። የኑሮ ውድነትንም አስመልክተው ሙያዊ ምክረ ሃሳቦችን ያጋራሉ።

May 20, 202416 min
For the best experience, listen in Metacast app for iOS or Android