SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ - podcast cover

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Last refreshed:
Follow this podcast in the Metacast mobile app to refresh it and see new episodes.
Download Metacast podcast app
Podcasts are better in Metacast mobile app
Don't just listen to podcasts. Learn from them with transcripts, summaries, and chapters for every episode. Skim, search, and bookmark insights. Learn more

Episodes

የውይይት መድረክ፤ አማራጭ መፍትሔዎችና ምክረ ሃሳቦች ለኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር በቪክቶሪያ / የኢትዮጵያውያን ማኅበር በቪክቶሪያ

ዶ/ር ቢቾክ ዋን፤ በቪክቶሪያ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስ መምህር፣ ደራሲ አዳሙ ተፈራ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፣ አቶ ዓለማየሁ በዛብህ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ዋና ፀሐፊ፣ አቶ አሕመድ ዳውድ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ሥራ አስፈፃሚና ቦርድ አባል፣ ደራሲ ታክሎ ተሾመ፤ የቀድሞው በታዝማኒያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ በመቋጫ የመወያያ አጀንዳነት አማራጭ መፍትሔዎችን ያመላክታሉ፤ ምክረ ሃሳቦችንም ለኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር በቪክቶሪያ / የኢትዮጵያውያን ማኅበር በቪክቶሪያ ይቸራሉ።

Jul 18, 202518 min

የውይይት መድረክ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር / የኢትዮጵያውያን ማኅበር በቪክቶሪያ ቦርድ ያስፈልገዋል ወይስ አያስፈልገውም?

ዶ/ር ቢቾክ ዋን፤ በቪክቶሪያ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስ መምህር፣ ደራሲ አዳሙ ተፈራ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፣ አቶ ዓለማየሁ በዛብህ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ዋና ፀሐፊ፣ አቶ አሕመድ ዳውድ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ሥራ አስፈፃሚና ቦርድ አባል፣ ደራሲ ታክሎ ተሾመ፤ የቀድሞው በታዝማኒያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ በተከታይ የመወያያ አጀንዳነት በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር / የኢትዮጵያውያን ማኅበር በቪክቶሪያ ያስፈልገዋል ወይስ አያስፈልገውም በሚል የመወያያ ነጥብ ላይ ግለ አመለካከታቸውን ያካፍላሉ።

Jul 18, 202521 min

የውይይት መድረክ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር / የኢትዮጵያውያን ማኅበር በቪክቶሪያ የገጠሙት ተግዳሮቶችና ያስከተሏቸው መዘዞች

ዶ/ር ቢቾክ ዋን፤ በቪክቶሪያ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስ መምህር፣ ደራሲ አዳሙ ተፈራ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፣ አቶ ዓለማየሁ በዛብህ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ዋና ፀሐፊ፣ አቶ አሕመድ ዳውድ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ሥራ አስፈፃሚና ቦርድ አባል፣ ደራሲ ታክሎ ተሾመ፤ የቀድሞው በታዝማኒያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ በተከታይ የመወያያ አጀንዳነት በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር / የኢትዮጵያውያን ማኅበር በቪክቶሪያ የገጠሙትን ተግዳሮችና ያስከተሏቸውን መዘዞች አስመልክተው ግለ አተያያቸውን ያንፀባርቃሉ።

Jul 18, 202520 min

የውይይት መድረክ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ከየት ተነስቶ የት ደርሷል?

ዶ/ር ቢቾክ ዋን፤ በቪክቶሪያ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስ መምህር፣ ደራሲ አዳሙ ተፈራ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፣ አቶ ዓለማየሁ በዛብህ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ዋና ፀሐፊ፣ አቶ አሕመድ ዳውድ፤ የቀድሞው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ሥራ አስፈፃሚና ቦርድ አባል፣ ደራሲ ታክሎ ተሾመ፤ የቀድሞው በታዝማኒያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ በቀዳሚ የመወያያ አጀንዳነት በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር የ38 ዓመታት ጉዞ በከፊል ነቅሰው ግለ አተያያያቸውን ያጋራሉ።

Jul 18, 202519 min

" እድር ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ዋስትናችን ነው " ፟ ወ/ሮ ቅድስት ሰለሞን የኢትዮጵያውያን የእድር መረዳጃ ማህበር በቪክቶርያ ጸሀፊ

የኢትዮጵያውያን የእድር መረዳጃ ማህበር በቪክቶርያ ባሳለፍነ ሰሞን አጠቃላይ የአባላት ስብሰባ ማድረጉ ይታወሳል ፡፡ የማህበሩ ሊቀመንበር ወ/ሮ ማህሌት ማስረሻ ፤ ወ/ሮ ቅድስት ሰለሞን ጸሀፊ እንዲሁም አቶ ዮናስ ደገፋ ገንዘብ ያዥ ፤ እድሩ ከነበረበት ተነስቶ በአሁን ሰአት ምን ደርጃ ላይ እንዳለ እና እና የወደፊት እቅዶቻቸውን በተመለከተ ሀሳባቸውን አጋርተውናል ፡፡

Jul 16, 20259 min

"ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የዘንድሮውን ዕንቁጣጣሽ አብረን ሲድኒ ላይ በትልቁ ለማክበር በናፍቆት እየጠበቅን በዝግጅት ላይ ነን" ወ/ሮ መሠረት አሰፋ

ወ/ሮ መሠረት አሰፋ፤ የ Habesha Spices and Events መሥራች፤ መጪውን የኢትዮጵያውያንን አዲስ ዓመት 2018 ቅበላና የኤርትራውያንን ቅዱስ ዮሐንስ በዓላት እንደምን በጋራ ድምቀትን በተላበሰ ሁኔታ ለማክበር መሰናዶ ላይ እንደሚገኙ ይገልጣሉ።

Jul 14, 20256 min

"በቦርድ መኖር ጥቅም እንጂ ጉዳት አላየንም፤ ቦርዱ የግድ መኖር አለበት የሚል ፅኑዕ እምነት አለን" አቶ ጋሻው አንለይ እና አቶ ታጠቅ መንጂ

በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ጋሻው አንለይና በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ቦርድ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ታጠቅ መንጂ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ማኅበር መተዳደሪያ ደንብ አፈፃፀም፣ በቦርድ አስፈላጊነት እና አላስፈላጊነት ላይ ያሉ አተያዮችን አስመልክተው አቋማቸውን ያንፀባርቃሉ።

Jul 14, 202528 min

"በእኛ በኩል በሽምግልናም ይሁን በጠቅላላ ጉባኤ ተገናኝተን የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ፈቃደኞች ነን" አቶ ጋሻው አንለይ እና አቶ ታጠቅ መንጂ

በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ጋሻው አንለይና በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ቦርድ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ታጠቅ መንጂ፤ ከማኅበር እስከ ቦርድ ምሥረታ የነበሩ ሂደቶችንና በቦርድና የማኅበሩ የሥራ አስፈፃሚ አባላት መካከል ተከስተው ያሉ የሥራ ግንኙነቶች መሻከርን አንስተው ይናገራሉ። የመፍትሔ ሃሳቦችንም ይቸራሉ።

Jul 13, 202530 min

First Nations representation in media: What’s changing, why it matters - በሚዲያ የነባር ዜጎች ውክልና፤ ምን ዓይነት ለውጥ እየተካሔደ ነው፤ ፋይዳውስ ምንድን ነው?

The representation of Indigenous Australians in media has historically been shaped by stereotypes and exclusion, but this is gradually changing. Indigenous platforms like National Indigenous Television (NITV) and social media are breaking barriers, empowering First Nations voices, and fostering a more inclusive understanding of Australia’s diverse cultural identity. Learning about these changes offers valuable insight into the country’s true history, its ongoing journey toward equity, and the ri...

Jul 12, 20259 min

አዲስ አበባ እንጦጦ ላይ የሚገኙትን የባሕር ዛፎች በሶስት ዓመታት ውስጥ በሀገር በቀል ዛፎች ለመተካት ዕቅድ መያዟን አስታወቀች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስጋትን፣ ግጭትን፣ ጥርጣሬንና አለመተማመንን የሚፈጥር ድርጊት ፈፅመዋል ያላቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ከምዝገባ እንዲሰርዝ ስልጣን የሚሰጥ አዲስ የአዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ለፓርላማ ቀረበ

Jul 06, 202515 min

ጎጆ የኢትዮጵያ ካፌና ሬስቶራንት ከሜልበርን - አውስትራሊያ 15 ምርጥ ካፌዎች አንዱ ሆኖ ተመረጠ

አቶ ዳንኤል አለማር፤ የጎጆ ካፌና ሬስቶራንት ባለቤት የቡናና ምግብ አቅርቦታቸው ለሽልማት የመጨረሻ ማጣሪያ ከቀረቡት 15 የሜልበር ምርጥ ካፌዎች አንዱ ለመሆን በመብቃቱ "የሬስቶራንቴ ስም 'ጎጆ የኢትዮጵያ ካፌ እና ሬስቶራንት'፤ ሀገርን ተሸክሞ ያለ ትልቅ ስም ያለው ነው። ሀገሬን በማስጠራቴ ትልቅ ኩራት ተሰምቶኛል" ሲሉ፤ እህታቸውና ሥራ አስኪያጅ መሠረት አለማር ፤ ሕልማቸው በዕጩነት ከ15 ምርጥ የሜልበርን ካፌና ሬስቶራንት ውስጥ አንዱ ለመሆን በመብቃት እንደማይገታ ይናገራሉ።

Jul 04, 202518 min

"ጠቅላላ ጉባኤ የጠራነው የፋይናንስ ሪፖርት ለማቅረብ፤ ለአሁኑና ወደፊትም ለሚመጣው ማኅበረሰብ የሚጠቅም የመተዳደሪያ ደንብ ክለሳ ላይ ለመነጋገር ነው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው

ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ለሰኔ 29 / ጁላይ 6 በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ለመላ የማኅበረስብ አባላት ስለቀረበው የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪና የመነጋገሪያ ዋነኛ አጀንዳዎች ያስረዳሉ።

Jul 04, 202524 min

"ፕሮፌሰሮቹ - መጽሐፍ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ፕሮፌሰሮች ያለፉበትን ሕይወት፣ ለሀገሪቱ ያላቸው ከፍተኛ ሚናና የኢትዮጵያን የታሪክ ገፅታ ለማሳየት የተፃፈ ነው" ተሾመ ብርሃኑ

ደራሲ ተሾመ ብርሃኑ ከማል፤ አዲስ ለሕትመት ባበቁት "ፕሮፌሰሮቹ" መጽሐፋቸው ስለምን ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፕሮፌሰሮች ሙያዊ አስተዋፅዖዎች ላይ ለማተኮር እንደወደዱ ይናገራሉ።

Jul 01, 202519 min

"ያስመረቅነው የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ለአማኞች አምልኮ ብቻ ሳይሆን ለማኅበረሰቡም ጭምር ነው" ፓስተር ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ

"በቤተ ክርስቲያንም ተከፋፍለን፣ በማኅበረሰብም ተከፋፍለን፣ በዘርም ተከፋፍለን ያሳለፍናቸው ምንም አልጠቀሙንም። አንድ ከሆንን፤ ከተባበርን፤ ከእዚህ በላይ መሥራት እንችላለን። ኅብረት የውስጥም የውጭም ጩኸቴ ነው!" አቶ ዳንኤል አለማር፤ በሜልበርን የዘፀዓት ኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ኅብረት አሠሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ

Jun 30, 202515 min

የዘጸአት የኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ህብረት ያሰራውን ህንጻ ቤ/ክ በመጪው ቅዳሜ ሊያስመርቅ ነው

አቶ ዳንኤል አለማር ከዘጸአት የኢትዮጵያውያን ወንጌላውያን ህብረት የህንጻ አሰሪ ሰብሳቢ ፤ በሜልበርን ከተማ በመጪው ቅድሚ የሚመረቀው የቤተክርስቲያን ህንጻ ፤ ህብረተሰቡ ከሌለው አቅሙ ቀንሦ ለትውልዱ እና ለመጪው ትውልድ ያሳነጸው ሲሆን ፡ በህንጻ አሰሪው ኮሚቴው ስም ምስጋናዪን አቀርባለሁ ብለዋል ። አያይዘውም በምርቃቱ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲገኙ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ።

Jun 24, 202511 min

ፕሬዚደንት ትራምፕ ኢራንና እሥራኤል ለተኩስ አቁም ተስማምተዋል ማለታቸውን ኢራን አስተባበለች፤ ከእሥራኤል በኩል ይፋዊ ምላሽ እየተጠበቀ ነው

የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን "ኢራን ውስጥ የሥርዓት ለውጥ ማድረግ ካስፈለገ በኢራን ሕዝብ እንጂ በቦምብ አይደለም" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስን የሥርዓት ለውጥ ዕሳቤ ተቹ

Jun 24, 20254 min
For the best experience, listen in Metacast app for iOS or Android