SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ - podcast cover

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Last refreshed:
Follow this podcast in the Metacast mobile app to refresh it and see new episodes.
Download Metacast podcast app
Podcasts are better in Metacast mobile app
Don't just listen to podcasts. Learn from them with transcripts, summaries, and chapters for every episode. Skim, search, and bookmark insights. Learn more

Episodes

" እንኳን ለኢድ አልፈጥር በአል አደረሳችሁ " ሼህ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር

በአገር ቤት ምንም እንኳን የሰላም ስጋቱም ሆነ የኑሮ ውድነቱ ህብረተሰቡን ለስጋት ቢጥልም ፤ የእስልምና እምነት ተከታዪች የረመዳን ጾምን በመረዳዳት አሳልፈው ፤ የኢድ አልፈጥር በአልን በደስታ እያከበሩ ነው ፤ ሲሉ በአገር ቤት የሚገኙት እና በአውስትራሊያ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሪ የሆኑት ሼህ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር ተናግረዋል» በአውስትራሊያ ለሚገኙት የእምነቱ ተከታዮችም የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አድርሰዋል።

Mar 30, 202510 min

"የተማረ የሰው ኃይል በበቂ ቁጥር አለማግኘትን በተግዳሮት፤ ለችግር ፈቺነት መብቃትን በስኬት እንመለከታለን" ዶ/ር አሥራት አፀደወይን

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር አፀደወይን "ምርጥ የምርምር ዩኒቨርሲቲ መሆንና ለራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲነት መብቃት የዩኒቨርሲቲያችን ርዕይ ነው" ይላሉ። የዩኒቨርሲቲውን 70ኛ፤ የአጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሉን 100ኛ ዓመት ክብረ በዓል ፋይዳና ታሪካዊ ምልከታ አንስተው ያስረዳሉ።

Mar 27, 202544 min

ጠ/ሚ አንቶኒ አልባኒዚ የመንግሥታቸው በጀት አማካይ ገቢ ላላቸው አውስትራሊያውያን 2500 ዶላር ያህል እንደሚያስገኝ ሲገልጡ የተቃዋሚ ቡድኑ የግብር ቅነሳውን አልደግፍም አለ

ፕሮዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የአስተዳደራቸው ከፍተኛ አመራር አባላት ወታደራዊ ዕቅዶችን በማኅበራዊ ሚዲያ ኧፕ መወያይትን አስመልክቶ ምልከታ እንደሚያደርጉበት አስታወቁ

Mar 26, 20259 min

"የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤታችን ወደ ቀድሞ ስሙ 'ተፈሪ መኮንን' እንዲመለስ አፅድቋል፤ ትልቅ ደስታ ላይ ነው ያለነው" ዶ/ር ብሥራት አክሊሉ

ዶ/ር ብሥራት አክሊሉ፤ የቀድሞ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ተማሪዎች ማኅበር ሰብሳቢ፤ የአሁኑ የእንጦጦ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ወደ መሠረተ ስያሜው ተፈሪ መኮንን እንዲመለስ የመወሰኑን ታሪካዊ ፋይዳዎችና የትምህርት ቤቱን 100ኛ ዓመት ለማክበር እየተደረጉ ስላሉ መሰናዶዎች ይናገራሉ።

Mar 24, 202521 min

የደብረ ዘይት በአል ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ከመምጣቱ በፊት የሚታዩ ምልክቶችን በተራራው ስብከቱ ያስተማረበትን ለማስታወስ የሚከበር በአል። "

ኢየሱስ ክርስቶስ በተራራው ስብከቱ የተነበያቸው ትንቢቶች በአብዛኛው እየታዩ ናቸው፤ የትንቢቱ መፈጸሚያዎች እንዳንሆን ወደ ንሰሀ መመለስ ይኖርብናል፤ የሚሉን በሜልበርን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ አገልጋይ የሆኑት መጋቢ ሓዲስ ብሩክ ተስፋዬ ናቸው ።

Mar 23, 202518 min

"መሬት ከፖለቲካ ወጥቶ ለኢኮኖሚው መሆን አለበት፤ አለመታደል ሆኖ የብሔር ፖለቲካ ከመሬት ጋር ተጣብቆ ተያይዟል" ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን

ዶ/ር ዳንኤል ካሣሁን - በኦስተን ኮሌጅ የጂኦ ስፔስ ተባባሪ ፕሮፌሰር፤ የመሬት ለአራሹ አዋጅ ግማሽ ክፍለ ዘመን መድፈን አስባብ አድርገው "የመሬት ለአራሹ አዋጅ፤ ዋዜማ፣ መባቻ፣ እና ማግሥት" በሚል ርዕስ ሰሞኑን ለሕትመት ስለአበቁት መጣጥፋቸው አንኳር ጭብጦች ያስረዳሉ።

Mar 22, 202517 min

ማኅበረሰባዊ የስንብት ቃል፤ "የዶ/ር እንግዳ ሕልፈት ለኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ትልቅ ጉድለት ነው" አቶ ሰለሞን ወንድሙ

በሜልበርን - አውስትራሊያ ነዋሪ የነበሩት ዶ/ር እንግዳወርቅ ለማ ዘላለማዊ ዕረፍት በኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት ዘንድ ጥልቅ ሐዘንን አሳድሯል። የቅርብ ጓደኞቻቸውና ብቸኛ ልጃቸው ጥልቅ የሐዘን ስሜታቸውን ይገልጣሉ። የዶ/ር እንግዳወርቅ የቀብር ሥነ ሥርዓት ቅዳሜ መጋቢት 13 / ማርች 22 በ Bulla Cemetery ዕኩለ ቀን ላይ ይከናወናል።

Mar 21, 202519 min

Cultural burning: using fire to protect from fire and revive Country - ባሕላዊ እሳት ልኮሳ፤ እሳትን በእሳት የመከላከል አጠቃቀምና ሀገራዊ ትድግና

Did you know that Indigenous Australians have been using fire to care for the land for tens of thousands of years? Evidence show that cultural burning practices not only help reduces the intensity and frequency of wildfires but also plays a vital role in maintaining healthy ecosystems. Experts share insights on the latest evidence behind this ancient practice. - የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ለአሥር ሺህ ዓመታት ያህል ለመሬት ክብካቤ ለማድረግ እሳት ይጠቀሙ እንደነበር ያውቃሉን? መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ባሕላዊ እሳት ልኮሳዎቹ ጠቀሜታዎቻቸው የደን ቃጠሎን መጠንና ድግግሞሽ መ...

Mar 20, 202510 min

" 'አፊኒ' ዕርቅ ማውረጃ፣ ግጭቶችን መፍቻና ቅድመ ግጭቶችን መከላከያ የሲዳማ ባሕላዊ ዕሴት ነው" አቶ ጃጎ አገኘሁ

አቶ ጃጎ አገኘሁ፤ የሲዳማ ክልል የባሕል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ፤ ሰሞኑን በቢሯቸው ተደግፎ በ21ኛው New African Film Festival ላይ ቀርቦ ስላለው "አፊኒ" ፊልም ፍቺ፣ ጭብጦችና ስኬቶች ይናገራሉ።

Mar 18, 202519 min

Want to help shape Australia’s future? Here’s how to enrol to vote - የአውስትራሊያን የወደፊት ዕድል መቅረፅ ይሻሉን? ድምፅ ለመስጠት እንደምን መመዝገብ እንደሚችሉ እነሆን

With another federal election due this year, there are steps you will need to take before casting your vote for the first time. Plenty of resources are available to help you enrol to vote and have your say in shaping our nation. - በእዚህ ዓመት ሌላ የፌዴራል ምርጫ ሊካሔድ ተቃርቧል፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፅዎን ከመስጠትዎ በፊት ሊከዉኗቸው የሚገቡ እርምጃዎች አሉ። ድምፅዎን በመስጠት የሀገራችንን የወደፊት ዕድል ለመቅረፅ ለምዝገባ እገዛ የሚያደርጉልዎ በርካታ ምንጮች አሉ።

Mar 13, 20257 min

"ኢትዮጵያዊ አንዱ ለሁሉ፤ ሁሉም ለአንዱ ይቆማል ከሚል ፅንሰ ሃሳብ፤ በኢትዮጵያዊነት ላይ መደራደር እፈልጋለሁ የሚሉ ምሁራን ያለበት ጊዜ ላይ ተደርሷል" ደራሲ መስፍን ማሞ

የ "አስራ ሰባት በአንድ" መጽሐፍ ደራሲ መስፍን ማሞ፤ ለስምንት ዓመታት የመጽሐፍ ቅኝት ያካሄዱባቸውን ስመ ጥር ኢትዮጵያውያን ደራሲዎችን የሕትመት ውጤት አንኳር ጭብጦች አንስተው ያመላክታሉ።

Mar 11, 202519 min

"የዘረኝነቱ ጣራ ዘመነ መሳፍንት ላይ ደርሷል" ደራሲ መስፍን ማሞ

የ "አስራ ሰባት በአንድ" መፅሐፍ ደራሲ መስፍን ማሞ፤ የማንነት ፖለቲካን አሉታዊ ተፅዕኖዎች ያነሳሉ፤ የፊስቱላ ሆስፒታል መሥራችና ሥራ አስፈፃሚ የነበሩትን የአውስትራሊያና ኢትዮጵያ ውድ ልጅ የሆኑቱን ዶ/ር ካትሪን ሃምሊንን ውርሰ አሻራዎች ሞገስ አላብሰው ይዘክራሉ፤ ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውን 'የእናት ካትሪን ቀን' ሰይመው በየዓመቱ በክብር እንዲዘክሯቸውም ምክረ ሃሳባቸውን ይቸራሉ።

Mar 11, 202522 min

"የሳይክሎን አልፍሬድ መምጣት በጣሙ አስፈሪ ነበር፤ ጥበቃውን ለእግዚአብሔር ነበር የሰጠሁት" ተዋናይት ሰናይት መብራህቱ

ሳይክሎን አልፍሬድ የተፈራውንም ያህል ባይሆን፤ ተዳክሞ በደረሰ ጉልበቱም ቢሆን ኩዊንስላንድና ኒው ሳውዝ ዌይልስ ላይ ጉዳቶችን አድርሷል። የብሪስበን ነዋሪዋ፤ የፊልም ተዋናይትና ዳይሬክተር ሰናይት መብራህቱ የሳይክሎኑ መምጣት ያሳደረባትን ሥነ ልቦናዊ ስጋትና የነበራትን ዝግጅት አስመልክታ ትናገራለች።

Mar 09, 20259 min

ዘላለማዊ ስንብት፤ ትዝታ ሰለሞን መስፍን

ፀሎተ ፍትሐትዋ በሜልበርን ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን፤ የቀብር ሥነ ሥነ ሥርዓቷ Bull Cemetery ቅዳሜ መጋኒት 6 ቀን 2017 / ማርች 15 ቀን 2025 የሚካሔደውን የወ/ሮ ትዝታ ሰለሞን መስፍንን ሕልፈተ ሕይወት ተከትሎ ከሀገር ቤት እህቶችዋ፣ ከማኅበረሰብ አባላት የቅርብ ወዳጆቿና የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር መሪ ጥልቅ ሐዘናቸውን ይገልጣሉ፤ ትውስታዎቻቸውንም ያጋራሉ።

Mar 08, 202521 min

የአለም አቀፍ ሴቶች ቀን በሜልበርን

ወጣት ማርታ ከበደ የዘንድሮውን የአለም አቀፉን የሴቶች ቀን ማርች 8 ፤ በሜልበርን የምንገኝ አፍሪካውያን እህትማማቾች ህብረት በአንድ ላይ ለማክበር ተዘጋጅተናል ብላናለች።

Mar 07, 20259 min

"አደራ ማለት የምፈልገው የዳያስፖራ አባላት በኢትዮጵያ ዕድል ተሳታፊም፣ ተጠቃሚም እንዲሆኑና ለሚታዩ ችግሮችም የመፍትሔ አካል እንዲሆኑ ነው" አምባሳደር ፍፁም አረጋ

አምባሳደር ፍፁም አረጋ፤ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር፤ መጪውን የኢትዮጵያና አውስትራሊያ 60ኛ ዓመት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አካትተው፤ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላትን ሀገራዊ ትስስሮሽ አሰናስለው ይናገራሉ።

Mar 06, 202519 min

"የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት፤ የዳያስፖራው ጠበቃ ሆኖ ጉዳያቸው በሀገር ውስጥ እንዲፋጠን፤ መፍትሔ እንዲያገኝ ይሠራል" አምባሳደር ፍፁም አረጋ

አምባሳደር ፍፁም አረጋ፤ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር፤ የአገልግሎቱን ዘርፈ ብዙ ሚናዎችና ተልዕኮዎች አስመልክተው ያስረዳሉ።

Mar 06, 202519 min

"ትውልዱ ለምንድን ነው በሀገሩ የሚዘባበተው? ለምንድን ነው ኢትዮጵያ ላይ እንዲህ የጨከነባት? በዘር የሚቧደነው?" ደራሲ መስፍን ማሞ

ደራሲ መስፍን ማሞ፤ የመፅሐፍ ዳሰሳ አካሂደው በ "አስራ ሰባት በአንድ" መድብል ያካተቷቸውን ደራሲዎች የሕትመት ውጤቶች አንስተው፤ ትውልዶችን በንፅፅሮሽ አጣቅሰው አተያያቸውን ያጋራሉ።

Mar 06, 202519 min

እጹብድንቅና ዓለምሰገድ ከበደ

የቤዝ ጊታር ተጫዋች አለምሰገድ ከበደ፤ ስለ ሙዚቃ ሕይወት ጅማሮውና አዲስ ስላወጣው "እጹብድንቅ" ሲዲው ይናገራል።

Mar 06, 20258 min
For the best experience, listen in Metacast app for iOS or Android