SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ - podcast cover

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Last refreshed:
Follow this podcast in the Metacast mobile app to refresh it and see new episodes.
Download Metacast podcast app
Podcasts are better in Metacast mobile app
Don't just listen to podcasts. Learn from them with transcripts, summaries, and chapters for every episode. Skim, search, and bookmark insights. Learn more

Episodes

ኃይሉ መርጊያ፤ ከጎጃም ማር ነሽ እስከ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መድረክ

"ከሙዚቃው ዓለም መውጣት አልፈልግም፤ የሚቻለኝን እያበረከትኩ መቆየት ነው የምሻው" የሚለው የኪቦርድና አኮርዲዮን ተጫዋች፣ ሙዚቃ አቀናባሪና ደራሲ ኃይሉ መርጊያ፤ ከ14 ዓመት የምድር ጦር ሙዚቀኛ ክፍል የልጅ ወታደርነት እስከ ምዕራቡ ዓለም - ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መድረክ እንደምን እንደገነነ ያወጋል።

Mar 04, 202516 min

ዮናስ የማነ፤ ከኦሎምፒያ ሠፈር ውልደት እስከ ሀገረ አውስትራሊያ ዘላለማዊ ዕረፍት

ከሶስት አሠርት ዓመታት በላይ አውስትራሊያን ሁለተኛ ሀገራቸው አድርገው የኖሩት አቶ ዮናስ የማነ ዘላለማዊ ዕረፍታቸውም እዚሁ ሆኗል። ቤተሰብና ወዳጆቻቸው የሕይወት ዘመናቸውን አንስተው ይዘክራሉ። የፀሎተ ፍትሐት ሥነ ሥርዓታቸው ቅዳሜ ማርች 1 ቀን 2025 / የካቲት 22 ቀን 2017 በሜልበርን ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ይካሔዳል።

Feb 28, 202519 min

"የአድዋ ድል ቋንቋችንና ባሕላችን ሳይጠፉ፣ ባንዲራችን ሳይረክስ፣ እምነቶቻችን ሳይደፈሩ አባቶቻችን ያቆዩልን የነፃነትና አንድነት መገለጫ ነው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው

ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ በማኅበሩ አዘጋጅነት ሜልበርን ውስጥ ስለሚከበረው 129ኛው የአድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ሥነ ሥርዓት ይናገራሉ።

Feb 26, 202514 min

The AI Election: How artificial intelligence impacted the world's biggest ballots - ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ምርጫ፤ ሰው ሠራሽ አስተውሎት እንደምን የዓለም ግዙፉ ምርጫ ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረ

From "Communist Kamala" to Bollywood endorsements, artificial intelligence and disinformation played a big role in some of the biggest democratic elections last year. - ባለፈው ዓመት ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) እና አሳስች መረጃ ከ "ኮሙኒስት ካማላ" እስከ ቦሊውድ ድጋፎች በተወሰነ መልኩ በግዙፉ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ላይ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።

Feb 25, 20258 min

"የይድነቃቸው ተሰማ ሶሻል ስፖርት ክለብ ፍቅር የበዛበት ትልቅ ቤተሰብ ነው፤ ከወንድም በላይ የሆኑ ጓደኞችን አፍርተንበታል" ሚካኤል አባተ

የይድነቃቸው ተሰማ ሶሻል ስፖርት ክለብ 7ኛ ዓመት አከባበርን አስመልክቶ የክለቡ መሪዎችና አባላት ምልሰታዊ ምልከታቸውንና የወደፊት ትልሞቻቸውን አንስተው ይናገራሉ።

Feb 25, 202513 min

"እኛ ኢትዮጵያውያን የመረዳዳት፣ የመተሳሰብ፣ የፍቅር ልዩ ፀጋ ያለን ሕዝብ ነንና እነዚህን በየዓመቱ አጠናክረን እንቀጥላለን" መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረሥላሴ ጎበና

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተባባሪነት የተዘጋጅውን "የታላቁ ጉዞና የቤተሰብ ቀን" አስመልክቶ፤ የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ፣ የአስተባባሪ ኮሚቴ አባልና ተሳታፊ የማኅበረሰ አባላት አተያያቸውን ያጋራሉ።

Feb 18, 202517 min

"ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች በማኅበራዊ ኑሮ፣ በኢኮኖሚና በፖለቲካውም ተሳስረው የኖሩ ናቸው፤ በጥቂት ልሂቃን ሰላማቸው ሊነካ አይገባም" ደራሲ ተሾመ ብርሃኑ ከማል

ደራሲ ተሾመ ብርሃኑ ከማል፤ በአንድ የአክሱም ትምህርት ቤት ሂጃብ የለበሱ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ወደ መማሪያ ክፍሎቻቸው ከመዝለቅ መታገዳቸውን አስመልክቶ በቅርቡ "የአክሱም ተማሪዎች የሂጃብ ጥያቄ የፖለቲካ ሕመሙ ምልክት ወይስ እራሱ ሕመሙ ነው?" በሚል ርዕስ ለሕትመት ስላበቁት መጣጥፋቸው ያስረዳሉ።

Feb 17, 202517 min

"መስቀልን የሚከተል መስቀል የማድረግ መብት እንዳለው ሁሉ፤ ሙስሊም የሆነች ሴትም ሂጃብ የማድረግ መብት አላት" ደራሲ ተሾመ ብርሃኑ ከማል

ደራሲ ተሾመ ብርሃኑ ከማል፤ በአንድ የአክሱም ትምህርት ቤት ሂጃብ የለበሱ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ወደ መማሪያ ክፍሎቻቸው ከመዝለቅ መታገዳቸውን አስመልክቶ በቅርቡ "የአክሱም ተማሪዎች የሂጃብ ጥያቄ የፖለቲካ ሕመሙ ምልክት ወይስ እራሱ ሕመሙ ነው?" በሚል ርዕስ ለሕትመት ስላበቁት መጣጥፋቸው ያስረዳሉ።

Feb 17, 202516 min

"የኤርትራ ሁለት ትናንሽ ከተሞች ግርዛትን ትተዋል የሚለው ሪፖርት ደስ የሚል ነው፤ ግርዛት የጠፋ ጎጂ ባሕል አይደለም" ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም

ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም፤ የሕዝብ ጤና ደህንነት አንቂ፤ ፌብሪዋሪ 6 / ጥር 29 የልጃገረዶችና ሴቶች ግርዛት የሚያስከትላቸውን አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት በመላው ዓለም በግንዛቤ ማስጨበጫ ቀንነት የማሰቡን ፋይዳዎች አስመልክተው ይናገራሉ።

Feb 06, 20259 min
For the best experience, listen in Metacast app for iOS or Android