SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ - podcast cover

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Last refreshed:
Follow this podcast in the Metacast mobile app to refresh it and see new episodes.
Download Metacast podcast app
Podcasts are better in Metacast mobile app
Don't just listen to podcasts. Learn from them with transcripts, summaries, and chapters for every episode. Skim, search, and bookmark insights. Learn more

Episodes

"በየዓመቱ የመሰባሰባችን ዓላማ በሜልበርን የሚገኙ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት እንዲተዋወቁ፣ እንዳይረሳሱና ወደ አንድነት እንዲመጡ ለማስቻል ነው" ኦቦ ተስፋዬ ደፋ

አቶ አብዱሰላም ሁሴን፤ በሜልበርን የኦሮሞ አረጋውያን በጎ አድራጎት ፕሬዚደንትና አቶ ተስፋዬ ደፋ፤ በሜልበርን የኦሮሞ አረጋውያን በጎ አድራጎት ፀሐፊ፤ ቅዳሜ ጥር 24 ከኦሮሞ ሲቪክ ድርጅቶች ፌዴሬሽን ጋር በጋራ ስላዘጋጁት የእራት ግብዣ ተልዕኮ ያስረዳሉ።

Feb 04, 20256 min

"የእግር ጉዞው ዓላማ ራቅ ባለው ዓለም የሚኖሩ ወገኖቻችንን በመንፈሳዊ፣ማኅበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ሀገራዊ ጉዳይም እንዲቀራረብ ማድረግ ነው"መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረሥላሴ

መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረሥላሴ ጎበና፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪና የሰሜን አፍሪካ ሃገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ፣ ዶ/ር ተፈሪ በላይነህ - በደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አገልጋይ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሶስተኛ ጊዘ ስላዘጋጀችው "ታላቁ የእግር ጉዞና የቤተሰብ ቀን" ዓላማና መርሃ ግብር ያስረዳሉ።

Feb 03, 202518 min

የአውስትራሊያ የዋጋ ግሽበት ዝቅ አለ

የአክሱም ወረዳ ፍርድ ቤት ያሳለፈውን የሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ዕገዳ የጣሱ ርዕሰ መምህራን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጠ

Jan 29, 20258 min

"የትም ሀገር ብንሆን ኢትዮጵያን ከውስጣችን ማውጣት አይቻልም፤በአፍሪካ የመጀመሪያው በሆነው የሰርከስ ማዕከል ግንባታ ኢትዮጵያውያን ተሳታፊ ቢሆኑ ደስ ይለኛል"ሶስና ወጋየሁ

የቀድሞዋ ኢትዮ - ሰርከስ ኮከብ አባልና የኢትዮ - ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሶስና ወጋየሁ፤ ከግለ ሕይወት ታሪካቸው ጋር አሰናስለው እንደምን ከሀገረ አውስትራሊያ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ፤ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሚሆነውን የሰርከስ ማዕከል በእንጦጦ ፓርክ በመገንባት ላይ እንዳሉ ይናገራሉ።

Jan 29, 202522 min

Celebrating, reflecting, mourning: Indigenous and migrant perspectives on January 26 - አከባበር፣ ምልሰታዊ ምልከታ፣ ሐዘን፤ የነባር ዜጎችና ፍልስተኞች የጃኑዋሪ 26 አተያይ

Some celebrate Australia Day with patriotic pride, others mourn and protest. What’s the right way to mark January 26, and can you have pride in your country while also standing against injustice? - የተወሰኑቱ የአውስትራሊያ ቀንን በአርበኛነት ስሜት ያከብሩታል፤ ሌሎች በፊናቸው በሐዘንና ተቃውሞ ያስቡታል። ጃኑዋሪ 26ን ተገቢ በሆነ መልኩ የማክበሪያ መንገዱ እንደምን ነው? ኢ-ፍትሐዊነትን ተፃርረው ቆመው ሳለ በሀገርዎ ላይ ኩራት ይሰማዎታልን?

Jan 21, 20258 min

"አባቶቻችን አንድ የሚያደርግ፤ የሚያሰባስብ ጥምቀትን ፈጥረውልናል፤ ልንጠብቀው የሚገባ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ዕሴት ነው" አቶ ሰለሞን በላይ

በዓለ ጥምቀት በሀገረ አውስትራሊያ ሜልበርን በድምቀት ተከብሮ አልፏል። የሜልበርን ነዋሪዎችን ጨምሮ ከተለያዩ የአውስትራሊያ ክፍለ አገራት የመጡ ኢትዮጵያውያን የበዓሉን መንፈሳዊና ማኅበራዊ ፋይዳዎች አስመልክተው አተያዮቻቸውን ያንፀባርቃሉ።

Jan 21, 20257 min

በሜልበርን የጥምቀት በአል እንዴት አለፈ ? በካህናት ዕይታ

መልአከ ፀሐይ ቀሲስ መንግሥቱ ኃይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የብሪስበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤እንዲሁም መጋቢ ምስጢር ቀሲስ ስንታየሁ አባተ፤ በምሥራቅ አውስትራሊያ አኅጉረ ስብከት የሜልበርን ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በካህናቱ እና ምእመናኑ የጋር ሥራ የተዋጣለት በዓል እንደነበረ ተናግረዋል ።

Jan 19, 202516 min

ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ ኢትዮጵያን ከራሷ ልጆች ማን ያድናታል?

ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ በከርተን ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብቶች ትምህርት ማዕከል ገዲብ ተመራማሪና መምህር ናቸው። ሰሞኑን የ2024 Fremantle Hungerford ሽልማት አሸናፊ ለመሆን የበቁበትን "Trials of Hope - የተስፋ ፈተና" የሥነ ግጥም መፅሐፋቸውን አስመልክተው ይናገራሉ።

Jan 19, 202518 min

"እንኳን ለበአለ ጥምቀቱ አደረሳችሁ ።"- ቀሲስ መንግስቱ ሀይሌ

መልአከ ፀሐይ ቀሲስ መንግሥቱ ኃይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የብሪስበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ ጥምቀት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፤ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሀንስ እጅ መጠመቁን የምታዘክረበት በአል ነው ብለዋል ።

Jan 17, 20259 min

የጥምቀት ዋዜማ፤ የሙዚቃ ድግስ በሜልበርን

አንጋፋውን ድምፃዊ ሻምበል በላይነህን ማዕከል ያደረገ፤ በሜልበርን ምርጥ ድምፃውያንና ሙዚቀኞች የታጀበ የሙዚቃ ድግስ ምሽት ስለመሰናዳቱ አስተባባሪው አቶ አበራ አያሌውና የጥበብ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ።

Jan 17, 20259 min

"ሕዝቤ የማያውቀውንና ከሕይወቱ ጋር ግንኙነት በሌለው የባዕዳን ሀገር ዕውቀትና ሀብት ራሴን ትልቅ አድርጌ ለማቅረብ የምሞክር ዘመናዊ ደንቆሮ አይደለሁም" ዶ/ር ይርጋ ገላው

ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ በከርተን ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብቶች ትምህርት ማዕከል ገዲብ ተመራማሪና መምህር ናቸው። ሰሞኑን የ2024 Fremantle Hungerford ሽልማት አሸናፊ ለመሆን የበቁበትን "Trials of Hope - የተስፋ ፈተና" የሥነ ግጥም መፅሐፋቸውን አስመልክተው ይናገራሉ።

Jan 16, 202513 min

"የተራቡትን ይመግብልን፣ የተበተኑትን ይሰብስብልን፣ በዓላችን የታይታ ሳይሆን የክብር በዓል ይሁንልን" መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ገሪማ

መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ገሪማ ተስፍዬ፣ የደብረ መድኃኒት መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪና የሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ፤ መልአከ ምሕረት ቀሲስ ዜናዊ ቸኮል፣ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ መል አከ ሕይወት ቀሲስ ሰናይ ዜና፣ የመካነ ሕይወት ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፤ በዓለ ጥምቀት የሚከበርበትን ዋነኛ ምክንያትና ፋይዳዎች አንስተው ይናገራሉ።

Jan 15, 202528 min

"ሰንደቁን እንደ አንድ ዋርካ ነው የምናየው፤ ሰውን በዘሩ፣ በሃይማኖቱ የማያርቅ ሰው ነው ያጣነው" አቶ መስቀሉ ደሴ

አቶ ሰንደቁ ተሰማ፤ በምዕራብ አውስትራሊያ - ፐርዝ ከተማ በታክሲ አገልግሎት ሥራ ላይ ተሠማርተው ሳለ፤ በፖሊስ ገለጣ መሠረት ሆን ብሎ መንገድ አሳብሮ በመጣ መኪና በደረሰባቸው የግጭት አደጋ ከጫኗቸው ሁለት ተሳፋሪዎቻቸው ጋር በ58 ዓመታቸው ከባለቤታቸውና ሶስት ልጆቻቸው ተነጥለው ከእዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

Jan 14, 202512 min

"በዓለ ጥምቀት በሃይማኖትም፣ በማኅበራዊም፣ እንዲሁም፤ ባሕልን አስጠብቆ ለትውልድ ለማውረስ ትልቅ ፋይዳ አለው" ቀሲስ አንተነህ ወርቁ

ቀሲስ አንተነህ ወርቁ፤ የሲድኒ ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ እና ዲያቆን ዳዊት ይርጉ፤ የሲድኒ ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና ሚዲያ ክፍል ኃላፊ፤ ስለ ዘንድሮው የሲድኒ በዓለ ጥምቀትና በዓለ ጊዮርጊስ አከባበር መርሃ ግብሮችና ትሩፋቶች ይገልጣሉ።

Jan 14, 202512 min

"የእኔ ሕልም ኢትዮጵያውያን ተስማምተው፤ በአንድነት ሀገራቸውን አሳድገው እኩልና ባለፀጋ እንዲሆኑ ነው፤ በሕይወት ዘመኔ ይኼ ሆኖ አያለሁ ብዬ አላስብም" አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ያለ ዝንፈት ሁሌም ውድ ሀገሬ ብለው በጠሯት የኢትዮጵያ ዕቅፍ ውስጥ ዳግም ላይመለሱ ለዘላለሙ ያረፉት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፤ ሀገራቸውን በምጣኔ ሃብት ባለሙያነት በምክትል የፋይናንስ ሚኒስትርነት፣ በዓለም አቀፍ መድረክ በዓለም ባንክና በተባበሩት መንግሥታት፣ በፖለቲካው መስክ ድምፃቸው ጎልቶ የሚሰማ የፓርላማ አባል ሆነው አገልግለዋል። በሕይወት ሳሉ ያካሔድነውን ቃለ ምልልስ በዝክረ መታሰቢያነት ደግመን አቅርበናል።

Jan 09, 202510 min
For the best experience, listen in Metacast app for iOS or Android