SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ - podcast cover

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Last refreshed:
Follow this podcast in the Metacast mobile app to refresh it and see new episodes.
Download Metacast podcast app
Podcasts are better in Metacast mobile app
Don't just listen to podcasts. Learn from them with transcripts, summaries, and chapters for every episode. Skim, search, and bookmark insights. Learn more

Episodes

"ጥረታችን የተፈሪ መኮንንን'ዕውቀት የሀገራችን መሳሪያ ናትና እንዳትጠብ እንድትሰፋ፤እንዳትወድቅ እንድትበረታ እንድትረዷት እለምናችኋለሁ'አደራ ለመፈፀም ነው"ዶ/ር ብሥራት

ዶ/ር ብሥራት አክሊሉ፤ የቀድሞ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ተማሪዎች ማኅበር ሰብሳቢ፤ በአሁኑ መጠሪያው የእንጦጦ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን ወደ ቀድሞ ስያሜው ተፈሪ መኮንን እንዲመለስ ማኅበራቸው እያደረጋቸው ስላሉት እንቅስቃሴዎች ያስረዳሉ። ትምህርት ቤቱ በሚቀጥለው ዓመት 100ኛ ዓመቱን ከማክበሩ በፊት መሠረተ ስያሜውን እንደሚያገኝ ያላቸውን ተስፋ ይገልጣሉ።

Oct 15, 202421 min

Indigenous astronomy: How the sky informs cultural practices - የነባር ዜጎች የሥነ ፈለግ ጥናት፤ ሰማይ እንደምን ባሕላዊ ትግበራዎች ያመላክታል

Astronomical knowledge of celestial objects influences and informs the life and law of First Nations people. - የሕዋ አካላዊ ቁሶች የነባር ዜጎች የሥነ ፈለግ ጥናት ዕውቀት ላይ ተፅዕኖን ያሳድራሉ፤ ሕይወትና ሕግንም ያመላክታሉ።

Oct 13, 202411 min

#21 Workplace conflict | Mind Your Health

Learn phrases you can use to resolve workplace conflict. Plus, find out where to access free content that can help you reduce the daily stress in your life.

Oct 09, 202412 min

"ተፈጥሮን ባልተንከባከብናት ቁጥር በእኛ ላይ ታምፃለች፤ፍልሰተኛው ማኅበረሰብ ተጎጂ እንደሆነ ሁሉ በታዳሽ ኃይል ተጠቃሚ መሆን አለበት" ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ

ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ የ renewaustraliaforall.org አስተባባሪ፤ ድርጅቱ ሰሞኑን በአውስትራሊያ ፓርላማ ተገኝቶ ስላቀረባቸው ረቂቅ ፖሊሲዎችና ለአውስትራሊያ ፍልሰተኛ ማኅበረሰብ አባላት ስለሚኖሩት ትሩፋቶች ያስረዳሉ።

Oct 07, 202419 min

ወ/ሮ ጽጌረዳ ዘለቀ የሲክስ ስታር ሆም ኤንድ ኮምዪኒቲ ኬር ዋና ሀላፊ ፤ የቤት ውስጥ እንክብካቤ በተመለከተ ልምዳቸውን አጋርተውና ፡፡

ወ/ሮ ጽጌረዳ ዘለቀ የሲክስ ስታር ሆም ኤንድ ኮምዪኒቲ ኬር ዋና ሀላፊ ፤ የቤት ውስጥ እንክብካቤ የሚያሻቸው ሰዎች ተገቢውን እገዛ ከመንግስት እንዲያገኙ ተገልጋዮች ማድረግ ያለባቸውን በተመለከተ ልምዳቸውን አጋርተውናል፡፡

Oct 02, 202418 min

" 'ሞቷል' የሚባለው በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር እንደተነሳ የምናሳየው የምንሠራቸውን ነገሮች በማሳየትና ተጠያቂም በመሆን ነው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው

ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ የማኅበረሰብ የበጎ ፈቃደኛ አገልጋይነትን ፋይዳዎች በማመላከት ጥሪዎችን ያቀርባሉ።

Sep 29, 202412 min

"በኢትዮጵያዊነታችን እናምናለን የምንል ከሆነ፤ የግል የፖለቲካ አቋማችንና ሃይማኖታችንን ሳናንፀባርቅ ወደ አንድነት እንምጣ" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው

ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ለማኅበረሰብ አገልጋይነት ገፊና ሳቢ የሆኗቸውን አስባቦች፤ በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅታችን ያወጉት 'ከጎንደር እስከ አውስትራሊያ' ግለ ታሪካቸው ተከታይ አድርገው ይናገራሉ።

Sep 29, 202414 min

" መስቀል ለአለም ክርስቲያኖች ሁሉ የማንነት መለያ ምልክት ነው። " -ብጹእ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር

ብጹእ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሀፊ ፤ የኒውዪርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የመስቀል በአልን ምክንያት በማድረግ በአውስትራሊያ እና በአለም ዚሪያ ለሚገኙ አማኒያን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ።

Sep 26, 202416 min

"የካንሰር በሽታ የሞት ፍርድ፣ እርግማን ወይም አለመታደል አይደለም" ዶ/ር ጅማ ሌንጂሳና አቶ ጥላዬ ተከተል

ዶ/ር ጅማ ሌንጂሳ፤ በደቡብ አውስትራሊያ አደላይድ የጡት፣ አንጀትና የማኅፀን ጫፍ የማኅበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ አስተባባሪና አቶ ጥላዬ ተከተል፤ በደቡብ አውስትራሊያ አደላይድ የጡት፣ አንጀትና የማኅፀን ጫፍ የማኅበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ አምባሳደር ስለ ቅድመ ምርመራ ግንዛቤ ማስጨበጫ የቅስቀሳ ዓላማና ግቦች ያስረዳሉ።

Sep 25, 202425 min

ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ ከጎንደር እስከ አውስትራሊያ

ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው የወቅቱ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት ናቸው። ከውልደት ሥፍራቸው ጎንደር ከተማ እንደምን ለሀገረ አውስትራሊያ እንደበቁ ግለ ታሪካቸውን አጣቅሰው ያወጋሉ።

Sep 24, 202416 min

ዝክረ መታሰቢያ፤ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ

በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ አራት ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በክልሉ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች በእኩልነት የሚሳተፉበት አዲስ የሲቪል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ጠየቁ

Sep 18, 202410 min

"አሉታዊ ነገሮችን ከሚያጎላው ጋር ሳይሆን፤ ቀና ከሚያስበው፣ መልካሙን ነገር ከሚያስታውሰን አካል ጎን መሆንን ነው የምሻው" ድምፃዊ ያደሳ ቦጂያ

"ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲለውጥ የምፈልገው አንዱ አሸናፊ ሌላው ተሸናፊ፤ አንዱ ሀገሩን የሚወድ ሌላው ሀገሩን የማይወድ ተደርጎ እንዳይታይ፤ ሁላችንም የሀገራችን ጠባቂና የሀገራችን ባለቤት መሆናችን ታውቆ ልባችን ቅን እንዲያስብ ነው" የሚሉት ያደሳ ቦጂያ፤ በመላው አፍሪካ የሚውለበለበው የአፍሪካ ኅብረት ሰንደቅ ዓላማ ዲዛይነር፣ ሰዓሊ፣ ድምፃዊና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ናቸው። ሰሞኑን አዲስ ስላወጡት "A World That I Want" ነጠላ የሙዚቃ ሥራቸው ያወጋሉ።

Sep 17, 202417 min

Can we fight misinformation without threatening our freedom of speech? - SBS Examines: የንግግር ነፃነታችንን ለስጋት ሳንዳርግ የተሳሳተ መረጃን መፋለም ይቻለናል?

There are calls to crack down on the sharing of misinformation online. But would this be an attack on free speech? - የኦንላይን የተሳሳተ መረጃ ስርጭትን በቁጥጥር ስር የማዋል ጥሪዎች እየቀረቡ ነው። ይሁንና ይህ በንግግር ነፃነት ላይ ጥቃት እንደመፈፀም ይቆጠራል?

Sep 17, 20245 min

"አንድነታችንን እናጠናክር፤ ባሕላችንን ለአውስትራሊያውያን እናስተዋውቅ፤ ብሩህ አዲስ ዓመት" - የደቡብ አውስትራሊያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ መሪዎች

ዶ/ር ለገሰ ጋረደው፤ በደቡብ አውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንትና ዶ/ር ተስፋሁን ጫኔ በአደላይድ - ደቡብ አውስትራሊያ ቅዳሜ መስከረም 11 / ሴፕቴምበር 21 ስለሚከበረው የአዲስ ዓመት መቀበያ ዝግጅት ይናገራሉ። የማኅበረሰቡ አባላትም በዝግጅቱ ላይ እንዲታደሙ የግብዣ ጥሪያቸውን ያስተላልፋሉ።

Sep 16, 202417 min
For the best experience, listen in Metacast app for iOS or Android