SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ - podcast cover

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Last refreshed:
Follow this podcast in the Metacast mobile app to refresh it and see new episodes.
Download Metacast podcast app
Podcasts are better in Metacast mobile app
Don't just listen to podcasts. Learn from them with transcripts, summaries, and chapters for every episode. Skim, search, and bookmark insights. Learn more

Episodes

"ጥላቻውና መገፋፋቱ ተወግዶ፣ በመላ ሀገራችን ሰላም ሰፍኖ ሕዝባችን ወደ ተረጋጋ ሕይወት የሚሸጋገርበት ዘመን ይሁንልን፤ እንኳን አደረሳችሁ" አምባሳደር ሀደራ አበራ አድማሱ

ሀደራ አበራ አድማሱ፤ በአውስትራሊያና ኒውዝላንድ የኢፌዴሪ ባለ ሙሉ ስልጣን፤ የ2017 አዲስ ዓመትን አስመልክተው ለኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ፤ መልካም ምኞታቸውንም ይገልጣሉ።

Sep 11, 20249 min

"የአባቶቻችን መታወቂያ ሰውን ማክበር፣ሰላምን ማረጋገጥ ነውና እኛ ኢትዮጵያውያን የአባቶቻችን ልጆች መሆናችንን ማስመስከር አለብን" መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሉ

መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሉ - በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የ2017 አዲስ ዓመት መልዕክት።

Sep 11, 20246 min

"መጠሪያዬ - ፍቅር፣ ተስፋ፣ አንድነና የሀገር ፍቅር ላይ የሚያጠነጥን፤ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን የተመኘሁበት አልበም ነው" ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ

ድምፃዊት ቬሮኔካ አዳነ፤ ከፍተኛ ሬኮርድ አስመዝግቦ የ17 ሚሊየን ብር ሽያጭ ስላስመዘገበው "መጠሪያዬ" የሙዚቃ አልበሟና የዘፈኖቿ ይዘቶች ትናገራለች።

Sep 10, 202421 min

"እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደርሳችሁ" የማኅበረሰብ መሪዎች - ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛውና ዶ/ር ለገሰ ጋረደው

ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅብረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንትና ዶ/ር ለገሰ ጋረደው በደቡብ አውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ የ2017 ዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክተው የመልካም ምኞት መልዕክቶቻቸውን ያስተላልፋሉ።

Sep 09, 20243 min

"መጪው ዓመት ሁላችንም የምንመኘውን የምናገኝበት አዲስ ዓመት እንዲሆንልን ምኞቴ ነው" ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና

ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ የግለ ታሪክ ወጉን የሚቋጨው የባሕር ማዶኛ የጥበብ ባለሙያዎች የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች በማንሳትና ለአዲሱ ዓመት 2017 ያለውን መልካም ምኞት በመግለፅ ነው።

Sep 09, 202417 min

ፍቅር ላይ መውደቅ፤ ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃናና ድምፃዊት ብፅዓት ስዩም

ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ ቀደም ባሉት የግለ ታሪክ ወጎቹ ከውልደት ቀዬው ተነስቶ የቲአትር መድረኮች ግዝፈቱ ላይ አላበቃም። ከቶውንም የቲአትር መድረክ ድምፃዊት ብፅዓት ስዩምን እንደምን የሕይወት ምሰሶው አድርጎ መርቆ እንደሰጠውና ለ26 ዓመታት አንዳቸው በአንዳቸው ውስጥ እየኖሩ እንዳለ አሰናስሎ ያወጋል።

Sep 08, 202426 min

"ከሎሬየት ፀጋዬ ገብረመድኅን ጋር መሥራት ትምህርት ቤት እንደመግባት የሚቆጠር ነው፤ ሙሉ ሰው ያደርጋል" ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና

ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ ቀደም ባሉት ሁለት ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቻችን ከውልደትና ዕድገቱ አንስቶ፣ በኢትዮጵያ የተውኔት ሕይወት መድረክ እንዴት እንዳበበት፤ የግለ ሕይወት ታሪኩን ነቅሶ በምናባዊ ምልሰት አጓጉዞናል። በቀጣዩ ዝግጅት አብቦና ጎምርቶ እንደምን መድረክ ላይ ግዘፍ እንደነሳ ቀንጭቦ ያወጋል።

Sep 03, 202413 min

Is the cost of living affecting social cohesion? - SBS Examines: የኑሮ ውድነት ማኅበራዊ ትስስር ላይ ተፅዕኖን ያሳድራል?

According to recent research, the biggest concern facing Australians today is the economy, and it’s causing ruptures within our society. - በቅርቡ በተካሄደ ምርምር መሠረት፤ በአሁኑ ወቅት አውስትራሊያን ገጥሟት ያለው ትልቁ ስጋት ምጣኔ ሃብት ነው። ሕብረተሰባችን ውስጥም ብርቱ ውጥረትን ፈጥሮ አለ።

Sep 02, 20244 min

"የአባቶች ቀን ለመላ አባቶች የልጆቻንን ሰብዕና በመልካም ጎኑ ለመቅረፅ ኃላፊነታችንን ለመወጣት አስበን የምንውልበት ቀን እንዲሆንልን እመኛለሁ" አቶ በፈቃዱ ወለሎ

በየዓመቱ ወርኃ ሴፕቴምበር በገባ በመጀመሪያው እሑድ ከፀደይ የዳግም ውልደትና ሕይወተ ተሃድሶ ባሕላዊ ታሪክ ጋር ተያይዞ በመላው አውስትራሊያ የአባቶች ቀን ይከበራል። አባቶችንና የአባት ተምሳሌዎችን ቤተሰብዓዊና ሀገራዊ አስተዋፅዖዎች አጣቅሶ ክብር ለመቸርና ሞገስ ለማላበስ። አቶ በፈቃዱ ወለሎም ግላዊና ቤተሰባዊ ትውስታዎቻቸውን አጣቅሰው ስለ አባቶች ቀን ፋይዳዎች ይናገራሉ።

Aug 31, 20249 min

“ሁለት ፍቅረኛሞች ለዕጮኛነት ወይም ለጋብቻ ከመድረሳቸው በፊት ከአንድ እስከ ሶስት ዓመታት አብረው ቢያሳልፉ ጥሩ ነው” - ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ

ዳግም የቀረበ፤ ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ - የናታን የጋብቻና ቤተሰብ ምክር አገልግሎት መሥራችና ሥራ አስኪያጅ፣ ደራሲ፣ የጋብቻና ቤተሰብ ምክር አገልግሎት ባለ ሙያ ስለ ቅድመ ጋብቻ የፍቅር ግንኙነቶች ይናገራሉ።

Aug 28, 202433 min

Embracing the wisdom of traditional Indigenous medicine - የነባር ዜጎችን ባሕላዊ መድኃኒት ጥበብ ሞገስ ማላበስ

Understanding and respecting Indigenous knowledge of medicine may be the key to providing more holistic and culturally sensitive care in today's healthcare setting. - የነባር ዜጎችን ባሕላዊ መድኃኒት ዕውቀት መረዳትና ከበሬታንም መቸር፤ ጥንቃቄ የተመላበት ክብካቤን ለሚሻው ሁሉን አቀፍ የዘመናዊው ጤና ክብካቤ አወቃቀር ቁልፍ ሊሆን ይችላል።

Aug 27, 20249 min

"በ'ውጫሌ ውል' ተውኔት መክፈቻና መዝጊያ ወቅት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ሲውለበለብ ከሕዝቡ ልብ ውስጥ ፈንቅሎ የወጣ የጋለ ሀገራዊ ስሜት ነበር" ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና

ተዋናይ፣ ደራሲ፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ በቀዳሚ ክፍለ ዝግጅታችን ውልደትና ዕድገቱን፣ የቀለም ትምህርትና የትወና ጅማሮውን ነቅሶ ግለ ታሪኩን በከፊል አውግቷል። ወደ ቀጣዩ ግለታሪክ ትረካው ያመራው እንደምን ከአንጋፋ የጥበብ ሰዎች ጋር ለመድረክ እንደበቃ በማንሳት ነው።

Aug 27, 202417 min

Why is sex and sexuality education taught in Australian schools? - SBS Examines: አውስትራሊያ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የወሲብና ወሲባዊነት ትምህርት የሚሰጠው ስለምን ነው?

Sex ed in schools is controversial, but experts say it's vital for young people to learn about their bodies, identities, and healthy relationships. Why are some parents concerned? - የትምህርት ቤቶች ወሲባዊ ትምህርት አወዛጋቢ ነው፤ ይሁንና ጠበብት የወጣቶች ስለ አካሎቻቸው፣ ማንነቶቻቸውና ጤናማ ግንኙነት መማር ወሳኝ እንደሁ ይናገራሉ። የተወሰኑ ወላጆች ስጋት ያደረባቸው ስለምን ነው?

Aug 22, 20245 min

"የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያው የሚያስከትለው የዋጋ ግሽበት ሀብትን ከፍተኛ ገቢ ላላቸው በተለይም ለነጋዴዎች ያሸጋግራል፤ ይህም በቅርብ ጊዜ የሚታይ ውጤት ነው" ዶ/ር ወርቁ አበራ

ዶ/ር ወርቁ አበራ፤ በዶውሰን ኮሌጅ የምጣኔ ሃብት ፕሮፌሰርና የምጣኔ ሃብት ዲፓርትመንት ሊቀመንበር በቅርቡ በኢትዮጵያ መንግሥት ግብር ላይ የዋለው "ውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያ" ፖሊስን አስመልክተው አተያይቸውን ያጋራሉ።

Aug 19, 202423 min

የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ሀገራዊ ምክክር ተወካዮች ሰንደቅ ዓላማን አካትቶ እስከ መገንጠል የሚፈቅደው የፌዴራል ሕገ መንግሥት አንቀፅ 39 እንዲሻሻል ምክረ ሃሳብ አቀረቡ

በእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረመድኅን የተመራው የሕወሓት ጉባኤ የድርጅቱን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 17 የማዕከላዊ አባላትን ማግለልና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርና የሕወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ ሰብሳቢነት እየተካሔደ ያለው ሌላኛው "ሕወሓትን መታደግ" ጉባኤ በሕወሓት መካከል ተከስቶ ያለውን ልዩነት አስፍቶ ቀጥሏል።

Aug 18, 202413 min

"ለመላ ኢትዮጵያውያን ለአዲሱ ዓመት የምመኘው አንድነትን ነው፤ አንድ ካልሆኑ ዕድገት የለም፤ አንድነት ኃይል ነው" እማማ አኒ ማርሴሩ አታሜይን

እማማ አኒ ማርሴሩ አታሜይን፤ ቦርቀው ያደጉባት፣ ፊደል የቆጠሩባት፣ ተኩለው የተዳሩባትንና ልጆች ያፈሩባትን ሀገረ ኢትዮጵያ ለቅቀው ከወጡ የአንድ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ዕድሜ አስቆጥረዋል። የኢትዮጵያ ፍቅረ ነበልባል ግና አሁንም ድረስ ልባቸው ውስጥ ይንቦገቦጋል፤ ትዝታዎቿም ዓመታት ሳያደበዝዟቸው ግዘፍ ነስተው ከአዕምሯቸው ተቀርፀው አሉ።

Aug 13, 202418 min
For the best experience, listen in Metacast app for iOS or Android