SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ - podcast cover

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Last refreshed:
Follow this podcast in the Metacast mobile app to refresh it and see new episodes.
Download Metacast podcast app
Podcasts are better in Metacast mobile app
Don't just listen to podcasts. Learn from them with transcripts, summaries, and chapters for every episode. Skim, search, and bookmark insights. Learn more

Episodes

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ አቡ ሴራ በዓመት ከ100 ሚሊየን በላይ መንገደኞችን የሚያስተናግድ የአውሮፕላን ማረፊያ ከተማ ሊገነባ ነው

ሕወሓት በምርጫ ቦርድ በልዩ ሁኔታ የተሰጠውን የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ እንደማይቀበል አስታወቀ፤ በሌላም በኩል ምርጫ ቦርድ ለሕወሓት የሰጠው የምዝገባ ማረጋገጫ በተጭበረበረ ማስረጃ የተመሠረተ በመሆኑ ምርመራ እንዲካሔድበት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንትና የሕወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ጠየቁ

Aug 11, 202413 min

"እመቤቴ ማርያም" የንስሐ ዝማሬ በሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ዘማሪያን

ዘማሪያን፤ ቤተልሔም ዘገየ ተፈራ፣ ሲካር ያሬድ፣ ደሊና ካሳሁን ላይችሉህ፣ አፎምያ ብስራት ታዬ፣ ቤቴል ጌታቸው ለገሰ፣ ኑኅሚን ወንድወሰን ክብረት፣ በጸሎት አስማረ ይታይህ፣ ማርያማዊት ጌታቸው ለገሰ፣ ማርያማዊት ገብረሕይወት ተፈሪ፣ ኤድና ብስራት ታዬ እና አርሴማ ተስፋዬ።

Aug 08, 20249 min

What is genocide? - SBS Examines: ዘር ማጥፋት ምንድነው?

'Genocide' is a powerful term — it's been called the "crime of crimes". When does large-scale violence become genocide, and why is it so difficult to prove and punish? - 'ዘር ማጥፋት' እጀግ ብርቱ ቃል ነው፤ "የወንጀሎች ወንጀል" ተብሏልም። የመጠነ ሰፊ አመፅ ክስተት የዘር ማጥፋት ድርጊት ሆኖ ሲገኝ እውን መሆኑን ለማረጋገጥና ቅጣትን ለመጣል በእጅጉ አዋኪ የሚሆነው ስለምን ነው?

Aug 06, 20246 min

"ብር እየወደቀና የዋጋ ንረት እየበዛ የሚያስቸግር ከሆነ፤ዋጋውን ለመቆጣጠር ያለችን ትንሽ ቁልፍ የወለድ መጠን መጨመር ነው፤ያ ደግሞ ምርታማነትን ይጎዳል" ዶ/ር ሙሴ ደለለኝ

ዶ/ር ሙሴ ደለለኝ አረጋ - በተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ጉባኤ በአፍሪካ መምሪያ የማምረት አቅምና ዘላቂ ልማት ንዑስ መምሪያ ኃላፊ፤ ሰሞኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግብር ላይ መዋሉን ስላስታወቀው "የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ማሻሻያ" ፖሊሲ የሚገጥሙትን ተግዳሮቶች፣ የሚያስከትላቸውን መዘዞችና ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ሊቀሰሙ የሚገቡ ልምዶችን ነቅሰው ምክረ ሃሳባቸውን ያጋራሉ።

Aug 04, 202422 min

"የውጭ ምንዛሪ ማስተካከያ ትልቁ ችግር ሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎችንም ማናጋት መቻሉ ነው፤በጀትን ጨምሮ ከታክስ፣ እስከ ወለድ መጠን ድረስ"ዶ/ር ሙሴ ደለለኝ

"ሚዲያ/ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መንግሥት ገንዘቡን ጣለ የሚለው ትክክል አይደለም። መንግሥት ገንዘቡን አይደለም የጣለው፤ ይደግፈው የነበረውን ብር ነው መደገፍ የተወው። በነፃ ገበያ እንዲወሰን ነው ያደረገው፤ ይህ ፖሊሲ ነው ብር እንዲወድቅ ያደረገው፤ ሁለቱን ለይቶ ማየት ያስፈልጋል" የሚሉት ዶ/ር ሙሴ ደለለኝ አረጋ - በተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ጉባኤ በአፍሪካ መምሪያ የማምረት አቅምና ዘላቂ ልማት ንዑስ መምሪያ ኃላፊ፤ ስለ አዲሱ የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያ ፖሊሲ ያስረዳሉ።

Aug 04, 202417 min

"በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማን ሐዘን ጥልቅ ነው፤የእርዳታ ፕሮግራም አዘጋጅተናል"አቶ ሚካኤል ፈለቀና አቶ በፈቃዱ ወለሎ

በምዕራብ አውስትራሊያ የጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት ተጎጂዎች ጊዜያዊ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፤ አቶ ሚካኤል ፈለቀና አቶ በፈቃዱ ወለሎ፤ በፐርዝ ከተማ ለእሑድ ሐምሌ 28 ስለተዘጋጀው ልዩ የእርዳታ ፕሮግራም ያስረዳሉ።

Aug 02, 20249 min

"ከ2011 ጀምሮ ኢትዮጵያ በአማካይ ከባሕር ማዶ ኢትዮጵያውያን ታገኝ የነበረው 4 ቢሊየን ዶላር በእዚህ የበጀት ዓመት 6.5 ቢሊየን ደርሷል" አቶ በላይነህ አቅናው

አቶ በላይነህ አቅናው፤ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር፤ አገልግሎቱ ለባሕር ማዶ ነዋሪ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ስለሚያበረክታቸው አስተዋፅዖዎች ያስረዳሉ።

Aug 02, 202418 min

"በግሌ በአደንዛዥ ዕፅ ሱስ የተነሳ ይህችን የምንወዳትን ሀገር የሚረከብልን ወጣት አናገኝ ይሆናል የሚል ስጋት ውስጥ ነው ያለሁት" ወ/ሮ ነኢማ ሙዘይን መሐመድ

ወ/ሮ ነኢማ ሙዘይን መሐመድ፤ የይመለከተኛል በጎ አድራጎት ድርጅት መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ የአዕምሮ ሕመምና አደንዛዥ ዕፅ ሱስ ምን ያህል ስር እንደሰደደ፣ የመንግሥት፣ የሕዝብ፣ የሃይማኖት መሪዎችና የባሕር ማዶ ነዋሪ ኢትዮጵያውያንን የትድግና ድርሻ ያነሳሉ። ለእገዛቸውም ጥሪና ምስጋና ያቀርባሉ።

Jul 30, 202421 min

"ለስደት ፍቅሩ የለኝም፤ አውስትራሊያ የመጣሁት አጋጣሚዎች ስላስገደዱኝ ነው፤ ወደ ኢትዮጵያ ሳልመለስ በፊት ወድጄው የኖርኩበት ሀገር ነው" ወ/ሮ ነኢማ ሙዘይን መሐመድ

ወ/ሮ ነኢማ ሙዘይን መሐመድ፤ ለአዕምሮ ሕመምተኞች አገልግሎት ሰጪ የሆነው ይመለከተኛል በጎ አድራጎት ድርጅት መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ናቸው። ከውልደትና ዕድገታቸው እስከ በጎ አድራጎት ድርጅት ምሥረታ ያለ የሕይወት ጉዟቸውን ነቅሰው ይናገራሉ።

Jul 28, 202415 min

"በጎፋ ዞን ከደረሰው ችግር ስፋትና ብዛት አንፃር ያሉ ድጋፎች በቂ ስላልሆኑ በሁሉም በኩል ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንጠይቃለን" አቶ ካሳሁን አባይነህ

አቶ ካሳሁን አባይነህ ሓጎስ፤ የጎፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ፤ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ ሳቢያ የደረሱትን የሕይወት ጥፋቶች፣ የአስከሬን ፍለጋ ሂደቶች፣ የሚያሹ አስቸኳይና ዘላቂ ልገሳዎችን አስመልክተው ይናገራሉ።

Jul 27, 20248 min

በደቡብ ኢትዮጵያ በደረሰ የመሬት ናዳ ሳቢያ ከ100 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚደንት ካማላ ሃሪስ፤ ከሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለ2024 ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ለመፎካከር የሚያስችላቸውን የዕጩ ምክትል ፕሬዚደንትነት መጠነ ሰፊ ድጋፍ እንዳገኙ ተመለከተ

Jul 23, 20243 min

"በዓለም አቀፍ ተቋም ግፊት የኢትዮጵያን የጥሬ ብር ምንዛሪ ግብይት አቅም መቀነስ አንገትን የመታነቅ ያህል ነው" ኢንጂነር አያሌው አስፋው

ኢንጂነር አያሌው አስፋው፤ ሉላዊ የገንዘብ ዝውውርን፣ ከአሜሪካን ዶላር ውጭ ዓለም አቀፍ ግብይት የማድረግ አዎንታዊና አሉታዊ ተፅዕኖዎችን አስመልክተው ይናገራሉ።

Jul 23, 202411 min

Is immigration worsening the housing crisis? - SBS Examines: ኢሚግሬሽን የቤት ቀውስን ያባብሳል?

Australia's facing a worsening housing crisis. At the same time, the number of overseas migrant arrivals is at its highest ever since records began. Is increased migration driving up housing and rental prices? - አውስትራሊያ የቤት እጥረት ቀውስ ተጋርጦባት አለ። በሌላም በኩል የባሕር ማዶ ፍልሰተኞች ቁጥር ሬኮርድ መመዝገብ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከቶውንም ከፍተኛውን ደረጃ ይዞ ይገኛል። የፍልሰተኞች ቁጥር መናር የቤት ግዢ / ግንባታና የኪራይ ዋጋዎች እንዲያሻቅቡ ያደርጋል?

Jul 21, 20244 min
For the best experience, listen in Metacast app for iOS or Android