ከማገብት እስከ ሕወሓት - አምባሳደር ስዩም መስፍን
በአሁኑ ወቅት በሕይወት የሌሉት የቀድሞው የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ስዮም መስፍን በሕይወት ሳሉ ከSBS አማርኛ ጋር ባካሔዱት ቃለ ምልልስ ከትጥቅ ትግል ጅማሯቸው ተነስተው፤ ከሕወሓት አመራር በፈቃዳቸው ስለምን እንደተሰናበቱ አስረድተው ነበር (የSBS 50ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ዳግም የቀረበ)።

በአሁኑ ወቅት በሕይወት የሌሉት የቀድሞው የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ስዮም መስፍን በሕይወት ሳሉ ከSBS አማርኛ ጋር ባካሔዱት ቃለ ምልልስ ከትጥቅ ትግል ጅማሯቸው ተነስተው፤ ከሕወሓት አመራር በፈቃዳቸው ስለምን እንደተሰናበቱ አስረድተው ነበር (የSBS 50ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ዳግም የቀረበ)።
የአማራ ክልል ዳኞች በፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊ ወይም አወዛጋቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በማናቸውም ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሃሳብ እንዳይሰጡ የሚከለክል ደንብ ፀደቀ
በ77 ዓመታቸው ከአንድ አሠርት ዓመት በፊት ከእዚህ ዓለም ከመለየታቸው በፊት የቀድሞው የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪ፣ ደራሲ፣ ጋዜጠኛና ዲፕሎማት ከነበሩት አምባሳደር ዘውዴ ረታ ጋር በሙያ ሕይወታቸው፣ የሥነ ፅሁፍ በረከቶቻቸውና ዲፕሎማሲ ዘርፍ ዙሪያ አተያያቸውን አጋርተውናል። የSBS 50ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግም ዳግም አቅርበነዋል።
የአውስትራሊያ ብሔራዊ ባንክ የወለድ መጠን ቀነሰ
በሜልበርን የኢሬቻ ቱሉ / አፍራሳ ክብረ በዓል አስተባባሪዎች ኦቦ ዓለማየሁ ቁቤ፣ ኦቦ በንቲ ሆሉቃና አደይቱ ሚደቅሳ የክብረ በዓሉን ፋይዳዎችና የአከባበር ሂደቱን አንስተው ያስረዳሉ።
ሰሞኑን በሀገር አቀፍ ደረጃ 'ከፊል' ያሉትን የሥራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ ያሉት የጤና ባለሙያዎች ያነሷቸው የደመወዝ፣ የጥቅማ ጥቅምና ምቹ የሥራ ሁኔታ ጥያቄዎቻቸው ምላሽ ካላገኙ 'ሙሉ' የሥራ ማቆም አድማ ሊያደርጉ እንደሚችሉ አሳሰቡ፤ የጤና ሚኒስቴር አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ።
"የፉትስክሬይ ሮታሪ ክለብ፣ በጎ ፈቃደኞች፣ የአውስትራሊያ የሕክምና ተቋማትንና ለ19ኛ ዙር የተለያዩ የእርዳታ ቁሳቁሶችን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ የወጪ ድጋፋቸውን የቸሩ ኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያን የማኅበረሰብ አባላትን በአውስትራሊያ ኢፌዴሪ ኤምባሲ ስም አመሰግናለሁ" አምባሳደር አንዋር ሙክታር መሐመድ
Learn how to talk about time. - Learn how to talk about time.
The migration system is complex and confusing. Experts say a lack of accessible support and credible information is leading to visa abuse. - የፍልሰት ሥርዓት ውስብስብና አደናጋሪ ነው። ጠበብት ተደራሽነት ያለው ድጋፍና ተአማኒነት ለአግባብ የለሽ የቪዛ ተፅዕኖ እንደሚያመራ ይናገራሉ።
በኢትዮጵያ የልጅነት እርግዝና 13 በመቶ መድረስ አሳሳቢ ሆኗል
ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚን ጨምሮ አዲሱ የሌበር መንግሥት ካቢኔ አባላት ቃለ መሐላ ፈፀሙ
'በሕገ ወጥ የማዕድን ቁፋሮና ዝውውር ውስጥ የክልሎችና የአካባቢ ባለስልጣናት እጆች አሉበት' አሉ የምክር ቤት አባላት
ወ/ት ሰላማዊት ወሰን ከብሪስበን "በተለይ ያለ አባት ልጆቻቸውን ላሳደጉ እናቶች 'እንኳን ለእናቶች ቀን አደርሳችሁ' ማለት እፈልጋለሁ" ሲሉ፤ ወ/ሮ ቤተልሔም ጥበቡ ከሜልበርን "እናትነትን በቃላት መግለፅ አይቻልም፤ እናትነት ትልቅ ስጦታ ነው" ይላሉ፤ ወ/ሮ ሜሮን ተስፋዬም "የእናቶችን ቀን ማሰብ የሚገባን በየዕለቱ ነው" በማለት የእናቶችና የእናት ተምሳሌዎችን የክብር መዘከሪያና ሞገስ ማላበሻዋን "የእናቶች ቀን" አስመልክተው የእናትና ልጅ ግለ ሕይወታቸውን አጣቅሰው ያጋራሉ። አቶ ኢዮብ ቀፀላም ከሲድኒ፤ ሀገር ቤት ለሚገኙት ውድ እናታቸው የእናቶች ቀን መልካም ምኞታቸውን ያስተላልፋሉ።
በመላው አለም ለምትገኙ እናቶች በሙሉ እንኳን ለእናቶች ቀን አደረሳችሁ ። " እናቶችን ማክበር ማለት ሰላምን መፍጠር ለእኩልነት መቆም ማለት ነው " በሚል መርህ የተነሳቸው አሜሪካዊቷ አና ጃርቪስ ቀኑ ሲከበር ዛሬም ድረስ የእናቶች ቀን እናት በመባል ትታወሳለች።
ቴዎድሮስ ተሾመ ከበደ፤ ፀሐፊ፣ ዳይሬክተርና ተዋናይ ነው። በቅርቡ ሰሞነኛ የነበረውን ዓባይ ወይስ ቬጋስ ፊልሙን 'የኢትዮጵያ ኔትፊሊክስ' ሲል በጠራው Habeshaview TV አማካይነት ለሕዝብ ዕይታ አቅርቧል። ስለ ፊልሙ ጭብጥ፣ በባሕር ማዶና ሀገር ቤት ያሉ የሩቅ ርቀት ፍቅርና ፈተናዎችን ከሌሎች ፈታኝ ማኅበራዊ የሕይወት ጉዞዎች ጋር አሰናስሎ ይናገራል።
ጋዜጠኛ ኤልያስ ጉዲሳ፤ ሀገር ቤት የጋዜጣና መፅሔት አሳታሚና ባለቤት ሆኖ ዘግቧል። በድምፅ ሰጪነትም ተሳትፏል። በኬንያ የስደት ሕይወቱም ድኅረ ምርጫ ያስከተላቸውን የሕይወት ጥፋትና የንብረት ውድመት ትኩረት ሰጥቶ ተመልክቷል። በሀገረ አውስትራሊያም ፍልሰተኛ ሆኖ የምርጫ ክንውኖች በቅርበት ተከታትሏል። የአውስትራሊያን ዜግነት ከተላበሰ ወዲህ ግና በሀገር አቀፍ ምርጫ የአውስትራያን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለመቅረፅና ለመገንባት በድምፅ ሰጪነት ቀጥተኛ የዜግነት ድርሻውን ሲወጣ የዘንድሮው የ2025 ፌዴራል ምርጫ የመጀመሪያው ነው። ምልሰታዊ ምልከታውን ከአሁናዊ ተሞክሮው ጋር አሰናስሎ ንፅፅሮሹን ያጋራል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ 86 አብላጫ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበሮችን ይዘው የሁለተኛ ዙር አስተዳደራቸውን ጀመሩ፤ የምርጫ ድምፅ ቆጠራው ሲጠናቀቅ የሌበር ፓርቲ የምክር ቤት ወንበሮች እስከ 90 ሊደርሱ እንደሚችሉ ግምት አለ።
የሊብራል ፓርቲ በሌበር ፓርቲ ዕጩ ድል ተነስተው የምክር ቤት ወንበራቸውን ያጡትን የቀድሞው መሪውን የመተካት ሂደት ጀመረ
የአውስትራሊያ ማዕድን አሳሽ አስካሪ ሜታልስ ኩባንያ በኢትዮጵያ ሥራ ጀመረ
የሌበር ዕጩዋ አሊ ፍራንስ፤ ፒተር ዳተንን ድል ነሱ
On election day the Australian Electoral Commission anticipates one million voters to pass through their voting centres every hour. Voting is compulsory for everyone on the electoral roll, so all Australians should familiarise themselves with the voting process before election day. - የአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን በምርጫ ዕለት በሰዓት አንድ ሚሊየን መራጮች በምርጫ ማዕከላት ውስጥ እንደሚያልፉ ግምት አለው። ምርጫ ከግዴታ ጋር ተያያዥነት ስላለው ማናቸውም አውስትራሊያውያን ከምርጫው ቀን በፊት ስለ ምርጫ ሂደቱ በቂ ግንዛቤ መጨበጥ አለባቸው።
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ የማኅበረሰብ አመራርና ግለ ተሞክሯቸውን አጣቅሰው ይናገራሉ።
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አመራር አባላት "ከአንድ የሥራ ዘመን ወይም ሶስት ዓመታት በላይ ማገልገል የለባቸውም" ይላሉ። ስለምን? አተያያቸውን ያጋራሉ።
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ስለ ማኅበሩ ወቅታዊ እንቅስቃሴዎች ያስረዳሉ።
የካናዳ ተቃዋሚ ቡድን መሪ የምክር ቤት ወንበራቸውን አጡ
የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን 'የትግራይ ሊብራል ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ' በሚል ስያሜ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ሊያቋቁም ነው።
የጋዛ ጦርነት ቅዳሜ ሜይ 3 በሚካሔደው የአውስትራሊያ ፌዴራል ምርጫ፤ በሁለቱ ዋነኛ ፓርቲዎች ሌበርና ሊብራል/ናሽናልስ ላይ አንዱ ዋነኛ የፖሊሲ ተፅዕኖ አሳዳሪ ጉዳይ ሆኗል።
ለተሽከርካሪዎች ኢንዱስትሪ ራሱን የቻለ የሥርዓተ ደንብ ረቂቅ ፖሊሲ እየተዘጋጀ ነው
The differing and diverse religious beliefs Australians hold will influence their vote this election. - አውስትራሊያውያን ይዘዋቸው ያሉት የተለያዩና ዝንቅ ሃይማኖታዊ እምነቶች በዘንድሮው ምርጫ ድምፅ አሰጣጣቸው ላይ ተፅዕኖን ሊያሳድርባቸው ይችል ይሆናል።
አውስትራሊያ ረጅም እድሜን የሚኖሩ ሰዎች አሉባት ከሚባሉ አገራት መካከል አንደኛዋ ናት ።በአማካኝ አንድ አውስትራሊያዊ የ83ተኛ የልደት በአሉን ያከብራል። ነገር ግን የአቦርጅናል እና ቶርስት ስትሬት አይላንደር ሕዝቦች ከተቀረው አውስትራሊያውያን የእድሜ ጣራ ጋር ሲነጻጸሩ የእድሜያቸው ጣሪያ በስምንት አመት አመት ያንሳል። ይህንንም ለመቀየር ክፍተትን ማጥበብ የሚለው ሀሳብ በብሄራዊ ደርጃ የተቀረጸ ነው። የቀደምት ነዋሪዎችን ጤና እና ደህንነት በማሻሻል ፤ ሌሎች ነባር ያልሆኑ አውስትራሊያውያን የሚኖሩቱን ጥራት ያለው ህይወት እና እድሎችን እንዲያጣጥሙ ማድረግ ይቻላል።