SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ - podcast cover

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Last refreshed:
Follow this podcast in the Metacast mobile app to refresh it and see new episodes.
Download Metacast podcast app
Podcasts are better in Metacast mobile app
Don't just listen to podcasts. Learn from them with transcripts, summaries, and chapters for every episode. Skim, search, and bookmark insights. Learn more

Episodes

"በ13ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ከሚባሉት ብሔረሰቦች መካከል አርጎባ ነበር" ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ

ደራሲ ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ፤ የ"ኩሽ እና ኩሻዊ፤ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ሃይማኖት እና ነገድ" መጽሐፍ ደራሲ፤ በኩሽና ኩሻዊነት ዙሪያ ያሉ ብዥታዎችን ያመላክታሉ። የማረቂያ ምክረ ሃሳቦችንም ይቸራሉ።

Dec 12, 202429 min

"ካለፈው ዓመት ዘንድሮ አንድነታችንን አጠንክረናል፤ ኢትዮጵያውያንን አነቃቅተናል" ወ/ት ገነት ማስረሻና አቶ አሕመድ ዳውድ

ወ/ት ገነት ማስረሻ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና አቶ አሕመድ ዳውድ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ንብረት ኃላፊ ዘንድሮ ከዲሴምበር 25 / ጥር 17 እስከ ዲሴምበር 29 / ጥር 21 ስለሚካሔደው 28ኛው የኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያን ዓመታዊ የእግር ኳስ ውድድር መሰናዶና ሂደት ይናገራሉ።

Dec 09, 202411 min

"ትንሽ ፊደል ቀመስን በሚለውም ውስጥ ኩሽና ኩሻዊነትን በተመለከተ ማደናገር አለ" ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ

ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ የሥነ ልሳን ተጠባቢ ናቸው። በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ታሪክ ዙሪያ የምርምር ግኝቶችን ያካተቱ ደርዘን የተጠጉ መፅሐፍትን ለሕትመት አብቅተዋል። ሰሞኑንም በኩሽ ዙሪያ በውዥንብር የታጨቁ ዕይታዎችን ለማጥራት በሚል ሙያዊ ኃላፊነት ዕሳቤ "ኩሽ እና ኩሻዊ" በሚል ርዕስ ከአንድ አሠርት ዓመት በላይ የፈጀ ጥናታዊ ሥራቸው የተካተተበትና የሁለት ዓመታት የጽሕፈት ጊዜያትን የወሰደባቸውን የአዕምሮ ጭማቂ የመጽሐፍ በረከታቸውን ለአንባብያን እነሆኝ ብለዋል። ከዶ/ር ግርማ ጋር ያካሔድነው ቃለ ምልልስ በእዚሁ አልተቋጨም። በቀጣዩ ክፍለ ዝግጅታችን የኩሽ ነገድ፣ ሀገረ መንግሥትና የመፅሐፍ ቅዱስን የኩሽ አጠቃቀም አንስተው ፍቺውን በማከል ያስረዳሉ።

Dec 08, 202415 min

"ኔልሰን ማንዴላን ከአንድ ሳምንት በላይ አስታመናል፤ ከእሥር ነው የወጡት ምንም የላቸውም በሚል 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ሰጥቻለሁ" የቀድሞው ፕ/ት መንግሥቱ ኃ/ማርያም

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት መንግሥቱ ኃይለ ማርያም የSBS አማርኛ እንግዳ ሆነው ለሁለት ጊዜያት ቀርበዋል። በቀዳሚነት ለደቡብ ሱዳን ነፃነትና ሉዓላዊነት የኢትዮጵያን አስተዋፅፆዎች በማስረዳት፤ ዳግም "ኢትዮጵያ ብቸኛ የነፃነት ኮከብ ሆና እንደኖረችና ከልጅነት ጀምሮ ኢትዮጵያን ሲያስቡ፣ ኢትዮጵያን እንደ ተስፋ ሲመለከቱ የኖሩ ሰው መሆናቸውን፤ በሂደትም የተገነዘቡትና ያዩትም ይህንኑ መሆኑን" ከእሥር እንደተፈቱ ያወጓቸው የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ኔልሰን ማንዴላ ዲሴምበር 5, 2013 የዛሬ 11 ዓመት ከእዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን አስመልክተው። የማንዴላን ዝክረ መታሰቢያ አስባብ አድርገን ቃለ ምልልሱን ደግመን አቅርበናል።

Dec 05, 202414 min

#76 Getting a gift (Med)

Learn how to talk about getting a gift for someone. Plus, find out what the Secret Santa tradition is all about.

Dec 04, 202413 min

የሜልበርን ኢሬቻ በዓል ነፃ አገልግሎት ሰጪ የማኅበረሰብ አባላት የብሩስ በጎ ፈቃደኞች ዕውቅና ሽልማት 2024 ተሸላሚ ሆኑ

የሜልበርን ኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት ኦቦ አብደታ ሆማ፣ ኦቦ ዳኜ ደፈርሻ፣ ኦቦ በንቲ ኦሊቃ እና አዴ ኢፍቱ ሚደቅሳ በተለይ በተከታታይ ለዓመታት ለኢሬቻ በዓል ትውውቅና አከባበር ላበረከቱት የማኅበረሰብ አገልግሎቶች የዘንድሮውን የብሩስ በጎ ፈቃደኞች ዕውቅና ሽልማት ከፌዴራል ኢሚግሬሽንና ዜግነት ረዳት ሚኒስትር ጁሊያን ሂል እጅ ተቀብለዋል።

Dec 03, 20249 min

ከኢትዮጵያ ባንኮች የተሰረቀው የገንዘብ መጠን ከአምናው 1 ቢሊየን ብር ዘንድሮ ወደ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ከፍ አለ

የገንዘብ ምንዛሪው ገበያ መር መሆን የሀገሪቱ ጥቅል ምርት ዕድገት በቀጣዮቹ ወራት በሶስት በመቶ እንዲቀንስ፤ የዋጋ ግሽበቱ ከ10 በመቶ በላይ እንዲጨምር እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶች ማኅበር አመላከተ

Dec 01, 202414 min

"በአፍሪካውያን ሴቶች ዘንድ የቅድመ እርግዝና እንክብካቤ አገልግሎቶች አጠቃቀም ዝቅተኛ ነው" በየነ መረሳ

በየነ መረሳ፤ በዲከን ዩኒቨርሲቲ የነርስነትና አዋላጅነት ትምህርት ቤት ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ፤ በቪክቶሪያ ነዋሪ በሆኑ አፍሪካውያን ሴቶች ላይ በማካሔድ ላይ ስላሉት የቅድመ እርግዝና ክብካቤ ጥናታዊ ምርምር ፕሮጄክት ያስረዳሉ።

Nov 27, 202417 min

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕ/ት ጌታቸው ረዳ "ወደ ስልጣን ሽኩቻ እንድንገባ ተገደናል፤ እንደ ሕወሓት መዳን ከፈለግን በእራሳችን እንጂ በውጭ ኃይሎች መሆን የለበትም" አሉ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሁንታ የተቸረውን 582 ቢሊየን ብር አክሎ የኢትዮጵያ 2017 በጀት ከ1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር በላይ ደረሰ፤ የመጪው ዓመት በጀት ከአሁኑ እንደሚበልጥ ተመለከተ።

Nov 26, 202412 min

በትግራይ ክልል ለሠራዊት ብተናና መልሶ ማቋቋም ሥራ የሚውል ከዓለም አቀፍ አጋር አካላት 60 ሚሊዮን ዶላር፤ ከፌዴራል መንግሥቱ አንድ ቢሊየን ብር መመደቡ ተገለጠ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካይሮ - ግብፅ በተካሔደው 56ኛው የአፍሪካ አየር መንገዶች ማኅበር አጠቃላይ ስብሰባ ላይ በዓለም አቀፍ አገልግሎት ዘርፍ "የዓመቱ ምርጥ አየር መንገድ" ሆኖ ለስምንተኛ ጊዜያት ሽልማት ተቀዳጀ

Nov 24, 202411 min

"በደቡብ አውስትራሊያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ዘንድ ባካሔድነው ጥናት የዕንቅልፍ ማጣት ችግር 40 ፐርሰንት ነው" ዶ/ር ዮሐንስ አዳማ መላኩ

ዶ/ር ዮሐንስ አዳማ መላኩ፤ በፍሊንደርስ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ሕክምና መካነ ተቋም ገዲብ ተመራማሪ፤ በተለይ በአደላይድ - ደቡብ አውስትራሊያ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎችን በተመለከተ በቡድን ስላካሔዱት የዕንቅልፍና አመጋገብ ጥናታዊ ምርምር ዓላማና ግኝቶችን ነቅሰው ያስረዳሉ። በደቡብ አውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ጋር በመተባበር ሂደትና ውጤቱንም ቅዳሜ ኖቬምበር 30 / ሕዳር 21 ለማኅበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እንደምን ለውይይት እንደሚበቃ ይገልጣሉ።

Nov 24, 202412 min

"መንገደኞች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የሚያገኙት መስተንግዶ ብቻ አይደለም፤ ባሕልም ነው" ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ ጉተማ

ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ ጉተማ የሲንጋፖር፣ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ ቀጣና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የአየር መንገዱን ሁነኛ ትልሞችና ትግበራዎች ያመላክታሉ።

Nov 20, 202418 min

"ርዕይ 2035 ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢያንስ ወደ ሶስት የአውስትራሊያ ከተሞች ለመብረር ወስኗል" ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ ጉተማ

ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ ጉተማ የሲንጋፖር፣ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ ቀጣና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ ስለ አውስትራሊያ የሥራ ጉብኝታቸው ተልዕኮና የአየር መንገዱን ውጥኖች አንስተው ያስረዳሉ።

Nov 20, 202413 min

"የተቃውሞ ሰልፍ ያካሔዱ ወገኖች በአማራ ክልል ተንቃሳቃሽ የሆኑ ኃይሎች ወጥ አመራር ፈጥረው ለውይይትና ድርድር ዝግጁ እንዲሆኑ ተፅዕኖ መፍጠር አለባቸው" አምባሳደር ሃደራ

በአውስትራሊያና ኒውዝላንድ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሃደራ አበራ አድማሱ፤ በዓለም አቀፍ አማራ ግብረ ኃይልና በሜልበርን የአማራ ኅብረት አስተባባሪነት በሜልበርን ከተማ የቪክቶሪያ ፓርላማና ፌዴሬሽን አደባባይ ያካሔዱትን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ የተነሱ ሀገራዊ ጉዳዮችን አስመልክተው የኢፌዴሪ መንግሥትን አተያይ ያንፀባርቃሉ።

Nov 18, 202411 min

"በአማራ ክልል የድሮን ጥቃትና ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም የአውስትራሊያ መንግሥት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና እንዲያደርግ እንጠይቃለን" አቶ ግርማ አካሉ

አቶ ግርማ አካሉ፤ የዓለም አቀፍ አማራ ግብረ ኃይልን በሜልበርን የአማራ ኅብረት አስተባባሪ፣ ወ/ሮ ትዕግሥት አበረ፤ የተቃውሞ ሰልፍ ተሳታፊና አቶ ዳዊት ይኩኑ፤ በሜልበርን ከተማ የቪክቶሪያ ፓርላማና ፌዴሬሽን አደባባይ ስለ አካሔዱት የተቃውሞ ሰልፍ ዓላማ ያስረዳሉ።

Nov 18, 202415 min

"በዘር መተዋወቅ ጥላቻን ነው ያመጣው፤ ወገን እንጂ ዘር አያስመካም፤ ከየትኛውም ዘር ሁኑ አንድ ወገን ነን" መጋቢ ሔኖክ ዓለማየሁ

መጋቢ ሔኖክ ዓለማየሁ፤ በሜልበርን ቤተ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ፤ ለሕትመት አብቅተው እሑድ ሕዳር 8 / ኖቬምበር 17 ለምርቃት ስላሰናዱት "እኔ ማነኝ?" መፅሐፋቸው ዋነኛ ጭብጦች ይናገራሉ።

Nov 13, 202414 min

The impacts of First Nations tourism - የነባር ዜጎች ቱሪዝም ተፅዕኖዎች

Are you seeking a truly impactful Australian travel experience? Whether you’re seeking wilderness, food, art or luxury, there are plenty of First Nations tourism adventure that you can explore, led by someone with 65,000 years of connection to this land. Not only will you deepen your experience, but you’ll help drive cultural and economic opportunities for First Nations communities. - እውነተኛ የሆነ አይረሴ የአውስትራሊያ ጉዞ ለማድረግ ይሻሉን? በሰዎች እምብዛም ያልተነካ፣ ምግብ፣ ሥነ ጥበብ ወይም ቅንጦት ይሁን፤ ከእዚህች ምድር ጋር የ 65,000 ዓመታት ቁር...

Nov 12, 202410 min

“ኢትዮጵያን የሁሉም ነገዶች ቤት ሆና ኖራለች፤ ትኖራለች፤ ክልላዊነትን ዝቅ ማድረግ ያስፈልጋል” ዶ/ር ደረሰ አየናቸው

ዶ/ር ደረሰ አየናቸው፤ የቀድሞው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ዲን፣ የታሪክ ተባባሪ ፕሮፌሰርና በኤይክስ ማርሴል ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ ዘመን የአፍሪካ ቀንድ ጥናትና ምርምር ፕሮግራም ተመራማሪ ፤ ለሕትመት ስላበቁት “ሰሎሞናውያን፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ታሪክ (1262 - 1521) ጭብጦች ይናገራሉ።

Nov 12, 202410 min
For the best experience, listen in Metacast app for iOS or Android