SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ - podcast cover

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Last refreshed:
Follow this podcast in the Metacast mobile app to refresh it and see new episodes.
Download Metacast podcast app
Podcasts are better in Metacast mobile app
Don't just listen to podcasts. Learn from them with transcripts, summaries, and chapters for every episode. Skim, search, and bookmark insights. Learn more

Episodes

"ኢትዮጵያውያን በብዛት መጥተው የስዕል ኤግዚቪሽኔን ቢመለክቱልኝ ደስ ይለኛል" ሰዓሊ ኦላና ዳመና ጃንፋ

አርቲስት ኦላና ዳመና ጃንፋ፤ ኢትዮጵያ ተወልዶ። የኖርዌይ ዜኘትን ተላብሶ፣ ከአውስትራሊያዊት ባለቤቱ ለልጅ አባትነት በቅቶ መኖሪያውያን ሜልበርን አውስትራሊያ ያደረገ ሰዓሊ ነው። "Too Much Drama" የሚለው የስዕል ኤግዚቪሽኑ ቅዳሜ ጁን 29 ተጋባዥ ታዳሚ እንግዶች ባሉበት የሚከፈት ሲሆን፤ ከጁላይ 2 እስከ ሴፕቴምበር 6 ድረስ በዳንዲኖንግ ክፍለ ከተማ ለሕዝብ ዕይታ ይበቃል።

Jun 27, 202411 min

Indigenous art: Connection to Country and a window to the past - የነባር ዜጎች ሥነ ስዕል፤ ሀገራዊ ቁርኝትና የትናንት መስኮትነት

Embracing their oral traditions, Aboriginal and Torres Strait Islander peoples have used art as a medium to pass down their cultural stories, spiritual beliefs, and essential knowledge of the land. - ቃለ ልማዶችን ሞገስ በማላበስ፤ የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ሥነ ስዕልን ባሕላዊ ወጎቻቸውን፣ መንፈሳዊ እምነቶቻቸውንና ስለ መሬታቸው ያላቸውን መሠረታዊ ዕውቀቶች የማሸጋገሪያ ተግባቦት አድርገው ተጠቅመውበታል።

Jun 27, 20249 min

የስደተኞች ሳምንት 2024፤ ድምፃዊ ኤልያስ የማነ "ኪዊ" - ከአፍሪካ ቀንድ እስከ እስያ ፓስፊክ

የዓለም የስደተኞች ቀን ከ2001 አንስቶ ወርሃ ጁን በገባ በ20ኛው ቀን ሲከበር፤ አውስትራሊያ ውስጥ ጁን 20ን አካትቶ ከአንድ ቀን መታሰቢያነት ዝለግ ብሎ ከጁን 16 እስከ 22 አንድ ሳምንት ደፍኖ ይከበራል። ይህንኑ አስባብ አድርገን ከሶማሊያ ተንስቶ፣ በኬንያና ኒውዝላንድ አቋርጦ አውስትራሊያ የሠፈረውን ድምፃዊ ኤልያስ የማነ "ኪዊ" ከቀደም የግለ ታሪክ ወጉ ቀንጭበን አቅርበናል።

Jun 21, 202419 min

"ሥነ ጥበብ የቡድን ሥራ ሲሆን፤ ፖለቲካውንና የሕብረተሰብን አስተሳሰብ መምራት ይችላል" ዘማሪ፣ ሰዓሊና ደራሲ ይልማ ኃይሉ

ዘማሪ፣ ሰዓሊና ደራሲ ይልማ ኃይሉ፤ ወደ ሀገረ አውስትራሊያ ስለመጡበት መንፈሳዊ አገልግሎቶችና ፕሮግራሞች ይናገራሉ። ምዕመናንም ሜልበርንና ሲድኒ በሚካሔዱት መንፈሳዊ ፕሮግራሞች ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን ያቀርባሉ።

Jun 21, 202414 min

"የትዳር አጋሬ ባትረዳኝ ኖሮ የጥበብ ሥራዬ አይቃናም ነበር" ዘማሪ፣ ሰዓሊና ደራሲ ይልማ ኃይሉ

ዘማሪ፣ ሰዓሊና ደራሲ ይልማ ኃይሉ፤ ለምዕመናን ስላበረከቷቸው መዝሙሮች፣ ለሕትመት ያበቋቸውን መፃሕፍትና ለዕይታ ያቀረቧቸውን የቅብ ጥበባዊ ሥራዎቻቸውን አንስተው ይናገራሉ። ለጥበባዊ ሕይወት ስኬታቸው የቤተሰባቸውን ሚና አንስተው ምስጋና ያቀርባሉ።

Jun 21, 202414 min

ኪነ ጥበብና ዲፕሎማሲ፤ የኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስ 120ኛው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጥበባዊ ተሃስቦ

በ1903 በዳግማዊ ምኒልክ ፊርማ መሠረቱ የፀናው የኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስ ይፋ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከኮሪያ እስከ ቀዝቃዛው ጦርነት፤ ከምጣኔ ሃብትና ረድዔት ድጋፍ እስከ ሰብዓዊ መብቶችና ዲሞክራሲያዊ ርዕዮተ ዓለሞች ተፈትኖ 120ኛ ዓመቱን አስቆጥሯል። ኪነ ጥበባዊ ትሩፋቶቹም እንደምን በመድረክ ተነስተው በኢትዮጵያውያን የጥበብ ባለሙያዎች አንደበት እንደተዘከሩ አርቲስት ዓለማየሁ ገብረሕይወት ነቅሰው ይናገራሉ።

Jun 20, 202418 min

Facing religious discrimination at work? These are your options - በመሥሪያ ቤትዎ የሃይማይኖት መድልዖ ገጥሞዎታል? አማራጭዎችዎን እነሆ

Australia is a party to the International Covenant on Civil and Political Rights, which provides extensive protections to religious freedom. However, specific legislated protections vary across jurisdictions. If you have experienced religious discrimination at work, it is important to know your options, whether you are considering submitting a complaint or pursuing the matter in court. - አውስትራሊያ ለሃይማኖት ነፃነት መጠነ ሰፊ ጥበቃዎችን የሚቸረው የዓለም አቀፍ ሲቪልና ፖለቲካዊ መብቶች ውል ፈራሚ ናት። ይሁንና፤ የተወሰኑ ድንጋጌያዊ ጥበቃዎች እንደ ስልጣነ...

Jun 19, 20248 min

73 መሥሪያ ቤቶችና 15 ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ከደንብና መመሪያ ውጪ የ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ግዢ መፈፀማቸው ተመለከተ

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በግለሰቦች ስም የባንክ ሂሳብ ከፍቶ ከ17 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡና ከእዚያም ውስጥ 9 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ለትርፍ ሰዓት ክፍያና የበዓል ስጦታ መዋሉ ተገለጠ

Jun 18, 202412 min

ፍቅርና አመፅ፤ 'ለምን ለቅቃ አትወጣም?' 'ለምን ኃላፊነትን አይወስድም?

ሲስተር ሰላም ተገኝ፤ በፐርዝ - ምዕራብ አውስትራሊያ የአፍሪካውያን ማኅበረሰብ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት፣ ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ በብሪስበን - ኩዊንስላንድ የደቡብ ማኅበረሰብ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተርና ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም፤ በሜልበርን - ቪክቶሪያ የሕዝብ ጤና ደህንነት አንቂ፣ የቤት ውስጥ ጥቃት / አመፅን ከኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማኅበረሰባት አኳያ አንስተው ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።

Jun 18, 202422 min

የቤት ውስጥ ጥቃት / አመፅ አማራጭ መፍትሔዎች ምንድን ናቸው?

ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም፤ በሜልበርን - ቪክቶሪያ የሕዝብ ጤና ደህንነት አንቂ፣ ሲስተር ሰላም ተገኝ፤ በፐርዝ - ምዕራብ አውስትራሊያ የአፍሪካውያን ማኅበረሰብ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንትና ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ በብሪስበን - ኩዊንስላንድ የደቡብ ማኅበረሰብ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተር፤ የቤት ውስጥ ጥቃት / አመፅን ከኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማኅበረሰባት አኳያ አንስተው ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።

Jun 18, 202418 min

እናቶቻቸው ላይ ጥቃት ሲፈፀም የማወዱ ኢትዮጵያውያን ወንዶች፤ ፍቅረኞቻቸውና ሚስቶቻቸው ላይ ጥቃቶችን አድራሽ የሚሆኑት ስለምን ነው?

ሲስተር ሰላም ተገኝ፤ በፐርዝ - ምዕራብ አውስትራሊያ የአፍሪካውያን ማኅበረሰብ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት፣ ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም፤ በሜልበርን - ቪክቶሪያ የሕዝብ ጤና ደህንነት አንቂና ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ በብሪስበን - ኩዊንስላንድ የደቡብ ማኅበረሰብ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተር፤ የቤት ውስጥ ጥቃት / አመፅን ከኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማኅበረሰባት አኳያ አሰናስለው ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።

Jun 16, 202413 min

የቤት ውስጥ ጥቃትን የሚረዱት እንደምን ነው?

ሲስተር ሰላም ተገኝ፤ በፐርዝ - ምዕራብ አውስትራሊያ የአፍሪካውያን ማኅበረሰብ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት፣ ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም፤ በሜልበርን - ቪክቶሪያ የሕዝብ ጤና ደህንነት አንቂና ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ በብሪስበን - ኩዊንስላንድ የደቡብ ማኅበረሰብ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተር፤ የቤት ውስጥ ጥቃት / አመፅን ከኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማኅበረሰባት አኳያ አሰናስለው ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።

Jun 15, 202413 min

ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ ፋርማሲ - የቤት ሽያጭና ግዢ

በፍሬድ ማየር ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ባለሙያዋ ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ ባለፉት ሁለት ክፍለ ዝግጅቶቻችን ከመሀል ሜዳ እስከ ሀገረ አሜሪካ ያለፉበትን የሕይወት ጉዞ አንስተው አውግተዋል። በውይይታችን መቋጫ ከፋርማሲ ሙያቸው ጎን በሲያትል ከተማ ተሰማርተው ስላሉበት የቤት ግዢና ሽያጭ (Real Estate) የንግድ መስክ ይናገራሉ።

Jun 14, 202412 min

"ሀገር ቤት ፋርማሲ ውስጥ በዝቶ የገጠመኝ የፋርማሲ ባለሙያ ያልሆኑ ሰዎች ናቸው" ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ

በፍሬድ ማየር - ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ባለሙያ ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ እንደምን ወደ ፋርማሲ ሙያ እንደዘለቁና በሙያው መስክ እንደተሠማሩ ያወጋሉ። የኢትዮጵያንና የአሜሪካ ፋርማሲዎች አሠራርን ነቅሰው ያስረዳሉ።

Jun 13, 202413 min

ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ ከመሃል ሜዳ እስከ ሀገረ አሜሪካ

ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ በፍሬድ ማየር - ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ባለሙያ ናቸው። ከመሀል ሜዳ ተነስተው ሀገረ አሜሪካ የዘለቁት የከፍተኛ ትምህርት ጥማታቸው ለማርካትና በላቀ ክህሎት ተጠብበው ሙያዊ አስተዋፅዖ ለማበርከት ተልመው ነው።

Jun 11, 202413 min

"በኢትዮጵያዊነቴ ኮርቻለሁ፤በሕይወት እያለሁ ይህን ክብር በማየቴ አመሰግናለሁ"ለማ ክብረት "በዝግጅቱ ኢትዮጵያዊነትን አይቼበታለሁ"የሺሐረግ ግርማ

ከአምስት ዓለም አቀፍ ፍፁም ቅጣት ምቶች አራቱን በማዳን የግብ ጠባቂ ሬኮርድ ያስመዘገበውና በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ኢትዮጵያ ሞሪሽየስን ለማሸነፍ እንድትበቃ ላስቻለው አንጋፋና ዝነኛው ለማ ክብረት ቅዳሜ ሰኔ 1 ቀን 2016 በሜልበርን - አውስትራሊያ የተካሔደው የዕውቅናና ምስጋና ምሽት ዝግጅት ተጠናቅቋል። ስኬቱም በኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ዘንድ የ"ይበልና ይቀጥል" ስሜትን አሳድሯል።

Jun 11, 202412 min
For the best experience, listen in Metacast app for iOS or Android