Great Truths Podcast (Amharic) - podcast cover

Great Truths Podcast (Amharic)

ዶ/ር ቤንጃሚን ዲንamharic.greattruthsglobal.org

This is the Amharic version of the Great Truths Podcast.

ይህ ፖድካስት የእግዚአብሔር ቃልን በተሻለ መንገድ ለመረዳት እና የመፅሐፍ ቅዱስን መልዕክት ዛሬ ለእኛ ምን እንደሆነ ለማወቅ ይረዳናል። ታላቅ እውነት (Great Truths) ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ ከ 10 ሚሊዮን በላይ የሆኑ የወንጌል አማኝ መሪዎችን (መጋቢዎች፣ እረኞች፣ ቄሶች፣ ሰባኪዎች፣ እና ወንጌላውያኖችን) ለማገልገል የሚፈልግ፣ ደግሞም በአለማችን ያሉ 660 ሚሊዮን ወንጌል አማኝ ክርስትያኖችን ከፍተኛ ጥራት ባላቸው የሚዲያ አማራጮች መፅሐፍ ቅዱስን ለማስተማር የሚሻ ተቋም ነው። ለበለጠ መረጃ እና የእያንዳንዱን ምዕራፍ ሙሉ መፅሐፍ ከተጨማሪ ግብዐቶች ጋር ለማግኘት ድህረ ገፃችንን ይመልከቱ https://amharic.greattruthsglobal.org/ 



Last refreshed:
Follow this podcast in the Metacast mobile app to refresh it and see new episodes.
Download Metacast podcast app
Podcasts are better in Metacast mobile app
Don't just listen to podcasts. Learn from them with transcripts, summaries, and chapters for every episode. Skim, search, and bookmark insights. Learn more

Episodes

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #4 | የትንሣኤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንበያና ታሪካዊ ዳራ (ክፍል 1)

በሉቃስ 24፥26-27 ባለው ክፍል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በርሱ ላይ ሊደርስ ስላለው መከራና ሥቃይ፣ እንዲሁም ከዚያ በኋላ ሊሆን ስላለው ክብር ተግባራዊነትና አስፈላጊነት በሙሴ፣ በነቢያትና በመጻሕፍት ሁሉ አስቀድሞ ስለመነገሩ ከትንሣኤው በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ተናግሮ ነበር።

Feb 15, 202522 minSeason 1Ep. 4

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #3 | የክርስቶስ ትንሣኤ ቀዳማዊ አስፈላጊነት

የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ የማይነጣጠሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶች፣ እንዲሁም የወንጌል መሠረትና ማእከል ቢሆኑም፣ ትንሣኤው ግን ቁልፍ ክሥተት ነው። ምክንያቱ ደግሞ ክርስቶስ በሕይወቱና በሞቱ የሠራቸው ነገሮች በሙሉ ግልጽ በሆነ መልኩ የሚታዪቱና በአማኞች ሕይወት ላይ ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉት በክርስቶስ የትንሣኤ አካል አማካኝነት ስለሆነ ነው። በመሆኑም፣ ትንሣኤ የሁሉም ነገር መሠረትና ማእከል ሲሆን፣ የክርስትና እምነት የመሠረት ድንጋይም ጭምር ነው።

Feb 15, 202525 minSeason 1Ep. 3

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #2 | ሞቱ ትንሣኤውን ይቀድማል

የክርስቶስ ኢየሱስ ትንሣኤ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ የነበረው ሕይወቱና አገልግሎቱ ማብቂያ ያገኘበት ክሥተት ስለመሆኑ ከወንጌላት ዘገባ መረዳት እንችላለን። በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ የዚህ እውነት ታሪካዊ ዳራውና ቀጥተኛ ዐውዱ የሰው ልጆች ሁሉ ሞት ሲሆን፣ በተለየ መልኩ ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ነው። የክርስቶስ ኢየሱስ ሞት የሰውን ልጆች ክፋትና ዐመፀ ጥግ የሚያሳይ ሲሆን፣ በሌላ ጎኑ ሲታይ ደግሞ የክርስቶስ መስቀል የሚያሳየው በሰዎች ኀጢአትና ዐመፅ ላይ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፍትሓዊ ፍርድ ነው።

Feb 15, 202524 minSeason 1Ep. 2

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ #1 | የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የእግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድ እና የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው

የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ ታሪክ በከፍተኛ ደረጃ የተገለጠ ተኣምራዊ ክሥተት ሲሆን፣ አስፈላጊነቱና ጥቅሙም እጅግ ከፍ ያለ ነው። ይህም ሊሆን የቻለው በአንድ አገር ወይም አህጉር ብቻ በተወሰነ መልኩ ሳይሆን፣ የክርስቶስን ማንነት የሰው ልጆችን ምንነት፣ የፍጥረታትን ሁኔታ እና የሰማይንና የምድርን አፈጣጠር ሁሉ ባጠቃለለ መልኩ ትርጉም ሊሰጥ በሚችልበት መንገድ ነበር። በዚህ ፖድካስት እንደምንመለከትው ክርስቶስ ራሱና የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች የክርስቶስ ትንሣኤ፣ ክርስቶስ የራሱን መለኮታዊ እና ሰብአዊ ማንነቱንና ያሳካቸውን ተግባራት በሙሉ በትንሣኤው ኀይሉ እንዳረጋገጠ እንገነዘባለን።

Feb 15, 202520 minSeason 1Ep. 1
Hosted on Buzzsprout
For the best experience, listen in Metacast app for iOS or Android